You are currently viewing “ፋኖ ነህ ብለው ከሰሱኝ፤ በአንድ ክስ 4 ጊዜ አሰሩኝ፤ …ይህ ሁሉ ግፍ የደረሰብኝ አማራ በመሆኔ ነው።” የቆዬ ሞላ_የኢትዮ ኬር በጎ አድራጎት ድርጅት የአማራ ክልል ቅርንጫፍ አስተባባሪ…

“ፋኖ ነህ ብለው ከሰሱኝ፤ በአንድ ክስ 4 ጊዜ አሰሩኝ፤ …ይህ ሁሉ ግፍ የደረሰብኝ አማራ በመሆኔ ነው።” የቆዬ ሞላ_የኢትዮ ኬር በጎ አድራጎት ድርጅት የአማራ ክልል ቅርንጫፍ አስተባባሪ…

“ፋኖ ነህ ብለው ከሰሱኝ፤ በአንድ ክስ 4 ጊዜ አሰሩኝ፤ …ይህ ሁሉ ግፍ የደረሰብኝ አማራ በመሆኔ ነው።” የቆዬ ሞላ_የኢትዮ ኬር በጎ አድራጎት ድርጅት የአማራ ክልል ቅርንጫፍ አስተባባሪ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 2/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ “ፋኖ ነህ ብለው ከሰሱኝ፤ በአንድ ክስ 4 ጊዜ አሰሩኝ፤ ፋኖ በመባሌ እስሩን በደሰታ ተቀበልሁት። ቅዱስ ዮሃንስ፣ በአባ ሳሙኤል እስር ቤት፣ ጥምቀትን በፔፕሲ እስር ቤት፣ ሰኔን በግራር ፖሊስ ጣቢያ እና በድጋሚ በፔፕሲ እስር ቤት አሳለፍኩ። ይህ ሁሉ ግፍ የደረሰብኝ አማራ በመሆኔ ነው። ከዚህ በታች አንድ ወንድሜ የላከልኝን ጽሁፍ እኔም የምጋራው እውነታ ስለሆነ እንሆ:_ ፋኖ እንደ አንበሳ ክንደ ብርቱ፣ እንደ ነብር ቁጡ፣ እንደ እርግብ የዋህ ነው። ፋኖ ቁሞ ከሚሸነፍ ሞቶ ማሸነፍን የሥነ ልቦናው መሠረት ያደረገ የአሸናፊነት ምልክት ነው። ፋኖ የዐማራ ሕዝብ ሥሪት ሕያው ምስክር፣ በራሳቸው የሚተማመኑ ሀገር እና ወገን ወዳድ ስመ ጥር ጀግና ኢትዮጵያዊያን የክብር ስም ጭምር ነው። ፋኖነት በሕይወት እና በሞት መካከል በሚደረግ ብርቱ ትግል የሚገኝ ወርቃማ ስም ነው። ፋኖነት የዕድሜ፣ የፆታ፣ የሃይማኖት፣ የብሔር፣ የቋንቋ፣ የሙያ፣ የዘር እና መሰል ልዩነቶችን ሳይፈጥርና ሳያጎል ሁሉም በተግባር ተመዝኖ በሚገለጥ እውነታ የሚገኝ እና ራሳቸውን ለሰፊው ሕዝብ ሲሉ አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች ክብር ስም ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply