You are currently viewing ፋኖ ነኝ የምትሉ፣ በፋኖነት የሰለጠናችሁ በሙሉ ህዝባችሁን የምትታደጉበት ጊዜው አሁን ነው! ነሐሴ 21/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) ፋኖ ማለት ለሕዝብ የቆመ እስከሆነ ድረስ  በጎጃም፣ በሸዋ…

ፋኖ ነኝ የምትሉ፣ በፋኖነት የሰለጠናችሁ በሙሉ ህዝባችሁን የምትታደጉበት ጊዜው አሁን ነው! ነሐሴ 21/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) ፋኖ ማለት ለሕዝብ የቆመ እስከሆነ ድረስ በጎጃም፣ በሸዋ…

ፋኖ ነኝ የምትሉ፣ በፋኖነት የሰለጠናችሁ በሙሉ ህዝባችሁን የምትታደጉበት ጊዜው አሁን ነው! ነሐሴ 21/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) ፋኖ ማለት ለሕዝብ የቆመ እስከሆነ ድረስ በጎጃም፣ በሸዋና በጎንደር የምትኖሩ ፋኖዎች ተነጋግራችሁ ወደ አስቸኳይ መፍትሔ መግባት ይኖርባችኋል። የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ የሚችሉትን እያደረጉ ናቸው። ለወንድሞቻችን የምንደርስበት ጊዜው አሁን ነው። በዚህ ጊዜ ለዚህ መከረኛ ህዝብ ልትደርሱት ይገባል፤ ፊት እየመራችሁ ወጣቱን ከኋላ እያስከተላችሁ ይህን ወራሪ ልንመክተው ይገባል። ይህን የምታደርጉት ለብልፅግና ወይንም ለማንም አይደለም አምጦ ለወለዳችሁ ህዝብ ስትሉ ነው። አውቃለሁ በዚህ ሥርዓት ታስራችኋል፣ ተሳዳችኋል፣ ያላስማችሁ ስም ተሰጥቷል፣ ይህ ሁሉ ግፍ የደረሰባችሁ ለዐማራ ህዝብ ስትሉ በመሆኑ ልትኩሩ ይገባል እንጂ “ብልፅግና …በደል አድርሶብናልና አንዋጋም” ብላችሁ ህዝባችሁ ለዳግም ባርነትና ስደት ሲዳረግ በዝምታ ማዬት የለባችሁም። እያያችሁ፥ እየሰማችሁ ነው እንቆምለታለን፣ እንሞትለታለን የምትሉት ህዝብ ዳግም በህወሓት ቅኝ ግዛት ሥር እየወደቀ ይገኛል። ይህን ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዜና ሰምታችሁ ያስችላችኋል ብዬም አላስብም። ህዝባችሁ በማንም ወራሪ ሲዋረድ፣ ሲታረድ፣ ሲፈናቀልና ሲደፈር “ቆሜ አላይም አሻፈረኝ” ብላችሁ ተነሱ። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አገዛዝ ያልተከፋ አልነበረም፥ በጣሊያን ወረራ ጊዜ ግን “የተቀያየምነው ከሥርዓቱ እንጂ ከህዝቡ ጋር አይደለም” በማለት ‘ኧረ ጥራኝ ጫካው’ እያሉ አርበኝነትን፤ ፋኖነትን በይፋ ጀምረው ህዝባቸውን ነፃ አውጥተውታል። እናተም የአባቶቻችሁን ገድል ድገሙት።እለምናችኋለሁ ፊት ሁናችሁ ምሩን እኛ እንከተላችኋለን። የሚያስፈልገውን ሎጂስቲክ እናቀርባለን። ከዚህ በኋላ ከብልፅግና መፍትሔ መጠበቅ ቂልነት ነው። ዛሬ ቆቦ፣ ነገ ወልድያ፣ ከዛ ሐይቅና ደሴ ተያዙ የሚል ዜና መስማት የሞት ሞት ነው። © ፋኖ ምሬ ወዳጆ

Source: Link to the Post

Leave a Reply