ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ነገ በባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ይቀርባል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ “ምልክታችን…

ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ነገ በባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ይቀርባል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ “ምልክታችን ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ነገ ጠዋት 3:00 ሰዐት ላይ ፍ/ቤት ይቀርባል።” ያለው የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል። “አሸናፊነታችን ግንባራችን ላይ የተጻፈ ዕጣ ፈንታችን ነው!” የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ክርክርን በሚመለከት ጠበቆች ባቀረቡት የክስ መቃወሚያ አግባብ ጉዳይ “ክሱ ውድቅ ለማድረግ” ወይም ደግሞ ” ክሱ በቀረበበት አግባብ ክርክሩ ይቀጥል” ለማለት የባህር ዳር ከተማና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ለነገ ህዳር 16/05/2015 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ሰዐት ቀጠሮ ሰጥቷል። በመሆኑም መላው የባህር ዳር ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች በፍ/ቤቱ በመገኘት የጀግናው መሪያችን ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን ችሎት እንከታተል ዘንድ ጥሪያችን እናስተላልፋለን። በተጨማሪም በባህር ዳር ከተማና አካባቢው የምትገኙ ንቁ የአማራ ወጣቶች አርበኛው ከሰባታሚት ማረሚያ ቤት ወጥቶ ፍ/ቤት ደርሶ እስኪመለስ አስፈላጊውን የንስር ዓይን ጥበቃና ክትትል እንድታደርጉ የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር የተለመደ ጥሪውን ያስተላልፋል። “ክፋት ለማንም ፤በጎነት ለሁሉም” አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል!

Source: Link to the Post

Leave a Reply