You are currently viewing “ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ፤ ምንም ዓይነት መፍትሄ በሌለው የፍ/ቤት ሂደት አልገኝም፤ የአማራ ህዝብ ነፃ ሲወጣ እኔም ነፃ እወጣለሁ!” በማለት ፍ/ቤት አይቀርብም።”…

“ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ፤ ምንም ዓይነት መፍትሄ በሌለው የፍ/ቤት ሂደት አልገኝም፤ የአማራ ህዝብ ነፃ ሲወጣ እኔም ነፃ እወጣለሁ!” በማለት ፍ/ቤት አይቀርብም።”…

“ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ፤ ምንም ዓይነት መፍትሄ በሌለው የፍ/ቤት ሂደት አልገኝም፤ የአማራ ህዝብ ነፃ ሲወጣ እኔም ነፃ እወጣለሁ!” በማለት ፍ/ቤት አይቀርብም።” የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) ከአርበኛ ዘመነ ካሴ ችሎት ጋር በተያያዘ ያቀረበው ጥሪ:_ በመጪው ሰኞ ታህሳስ 24/2015 ዓ.ም የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ የፍ/ቤት ቀጠሮ ነው። ነገር ግን ጀግናው አርበኛ ዘመነ ካሴ በእዬ ግሮሰሪ ቤት ለሚዶልቱት ፥ለሚያሴሩት የሃሰት ክስ (የግሮሰሪ የሃሰት ዶሴ) ፍ/ቤት መገኘት ተገቢ አይደለም ብሎ ፍ/ቤት መገኘት አቁሟል። በመሆኑም ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ፤ምንም ዓይነት መፍትሄ በሌለው የፍ/ቤት ሂደት አልገኝም “የአማራ ህዝብ ነፃ ሲወጣ እኔም ነፃ እወጣለሁ!” በማለት ፍ/ቤት አይቀርብም። ስለሆነም ለባህር ዳር ከተማና አካባቢው ለምትገኙ የአማራ ወጣቶች እንዲሁም ነዋሪዎች ሰኞ ጠዋት ጀምሮ በሰባታሚት ማረሚያ ቤት በመገኘት ለምልክታችን ፣ለመሪያችን እና አርዕያችን ለሆነው ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ያለንን ፍፁማዊ አጋርነት እና አንድነት እንገልፅ ዘንድ ጥሪያችን እናስተላልፋለን ። በግፍ እስር ፣አፈና ፣ማሳደድ እንዲሁም ማዋከብ የሚቆም ፥የተጀመረ የአማራ ትግል የለም። የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ። በመጨረሻም አርበኛ ዘመነ ካሴ በግፍ እስር ላይ ከሆነበት ዕለት ጀምሮ በቀን በቀን ሰባታሚት ማረሚያ ቤት በመገኘት ለምትጠይቁ ንቁ ፣ብርቱ እና አይበገሬ የከተማችን አማራ ወጣቶች ክብርና ምስጋና ይድረሳችሁ። በተጨማሪም አርበኛውን በጋራ በመሰብሰብ የመጠየቅ አኩሪ ተግባር ለፈፀማችሁ አስተዋይ የባህር ዳር ከነማ ደጋፊዎች ላቅ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ። በአጠቃላይ አርበኛውን ሰባታሚት የምትጠይቁ ከአራቱም አቅጣጫ የመጣችሁ ፥የምትመጡ ወገኖች ሁሉ የአማራ ወጣቶች በባህር ዳር ላደረጋችሁት ፣ለምታደርጉት ሁሉ ከፍተኛ ምስጋናውን ይገልፃል ። አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል ፤አማራነት ያሸንፋል!

Source: Link to the Post

Leave a Reply