You are currently viewing “ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ  <> ያስተማረን አርአያችን ነው!!!”  የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

“ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ <> ያስተማረን አርአያችን ነው!!!” የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

“ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ <> ያስተማረን አርአያችን ነው!!!” የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር ስለፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ የባህር ዳር እና አካባቢው ፍትህ ፈላጊ ወጣቶች፣ ነዋሪዎች በባህር ዳር ከፍተኛ ፍ/ቤት ተገኝተው አማራዊ አክብሮት ፣አድናቆት ፣ህብረትና አንድነት እንዲሁም ፍፁም አጋርነታቸውን እንዲገልጹ ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ ከፍ ያለ ምላሽ እያገኘ መሆኑ ግልጽ ነው። ማህበሩ ስለፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ካነሳቸው ዐበይት ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:_ 1) ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ለአዲሱ አማራ ትውልድ የትግል ምልክት ፣ለነፃነት ለምናደርገው የህልውና ትግል ፥ለነፃነት ችቦ ለኳሽ እና በአዲሱ አማራ ትውልድ ፥በአዲስ አሰተሳሰብ በርካታ ሚሊዮን ጀግና የአማራ ወጣቶችን ከጎኑ ያሰለፈ የትግል መሪ ነው። 2) ጀግናው አርበኛ ዘመነ ካሴ ለአዲሱ የአማራ ትንታግ ትውልድ ፥የአማራ ወጣት <> የትውልዱ አርአያ ነው። 3) አዲሱ የአማራ ትውልድ እንደ ጀግኖች ፋኖ ጎቤ መልኬ(ዋዋ) ፣ፋኖ አስቻለው ደሴ ፣ፋኖ ኤፍሬም አጥናፉ ፣ፋኖ ሞላ ደስዬ ፣ፋኖ አሸናፊ አለሙ ወዘተ…..<>ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል መከፈል ያለበትን መስዕዋትነት ሁሉ ለመክፈል የተዘጋጀን እልፎች ነን። 4) የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ፣እኩልነት እና ፍትህ ነው። የተደራጀ፣ የተቀናጀ እና የተናበበ ህዝባዊ ትግል ማሸነፉ አይቀሬ ነው! መላው የሲቪክ አደረጃጀቶች/ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎችም ውግንነታቸውን ለእውነት በማድረግ የጋራ እና የተናበበ አጀንዳ በመቅረጽ ለዘላቂ እና መሰረታዊ ለውጥ ታግሎ ማታገል ወገናዊ እና አደረጃጀታዊ ግዴታቸው ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply