You are currently viewing ፋኖ እስራኤል እሸቴ ከእስር ተለቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ/ም           አዲስ አበባ ሸዋ ህዳር 7/2015 ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ኮምቦልቻ ላይ ተይዞ…

ፋኖ እስራኤል እሸቴ ከእስር ተለቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ህዳር 7/2015 ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ኮምቦልቻ ላይ ተይዞ…

ፋኖ እስራኤል እሸቴ ከእስር ተለቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ህዳር 7/2015 ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ኮምቦልቻ ላይ ተይዞ አሰናግር ክ/ከተማ ባለ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው ፋኖ እስራኤል እሸቴ በሰው ዋስትና መፈታቱን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከስፍራው አረጋግጧል። የምስራቅ አማራ ፋኖ ምክትል አዛዥ በመሆን ታግሎ ሲያታግል የነበረው እስራኤል እሸቴ አቶ ስለሽ በተባለ የደህንነት አካል ከታሰረ በኋላ ህዳር 8/2015 ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ በሰው ዋስትና ከእስር ተለቋል። ከአሁን ቀደም በአንድ ሚዲያ ተናግሮት ነበር በተባለ የግል እይታው ለመታሰር መብቃቱ ተነግሯል። በኢትዮጵያ ዜጎች ሀሳባቸውን የመግለጽ መብታቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈተነ መሆኑ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። ጋዜጠኞች፣የማህበረሰብ አንቂዎች፣ፖለቲከኞች፣ ፋኖዎች እና ሌሎች በርካታ የህ/ሰብ ክፍሎችም ብዙውን ጊዜ ለእስር እየተዳረጉ ያሉት በአብዛኛው ከመናገራቸውና ከመጻፋቸው እንዲሁም ከመደራጀት እና ከመሰብሰብ ጋር በተያያዘ መሆኑን ስንመለከት ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይ ከፍተኛ የሆነ ያልተሻገርነው ስርዓት ወለድ ችግር እያጋጠመ ስለመሆኑ አመላካች ነው። የሸዋ ፋኖ አመራርና አባል የነበረዉ ፋኖ አካላቴ ታደሰና ፋኖ ሱራፌል ገብረሀናም በገንዘብ ዋስትና መፈታታቸው ታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply