“…ፋኖ የሚታገለው አባቶቻችን ያቆዩልንን ሀገር አቆይቶ ለልጅ ልጅ ለማስተላለፍ ነው>> ነው ሲሉ የፋኖ ሻለቃ መሪ አርበኛ ስጦታው ዳኘው (ባሻ) ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

“…ፋኖ የሚታገለው አባቶቻችን ያቆዩልንን ሀገር አቆይቶ ለልጅ ልጅ ለማስተላለፍ ነው>> ነው ሲሉ የፋኖ ሻለቃ መሪ አርበኛ ስጦታው ዳኘው (ባሻ) ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ክብራቸውን አያስነኩም፣ የሰው ክብር አይነኩም፣ ለክብር ይዘምታሉ፣ለሀገር ይሞታሉ፣ ለወገን መከታ ይሆናሉ። ተክፍቶ ማደር፣ በነፃነት መደራደር አይሆንላቸውም። ነፃነት ሲደፈር፣ ሀገር ሲወረር፣ ሕዝብ በጠላት ሲወጠር፣ ጠመንጃቸውን ወልውለው፣ ካርታቸውን ሞልተው፣ ካዝናቸውን አንዠርገው፣ ሳንጃቸውን ስለው ሀገር ተደፈረች ወደተባለበት ሥፍራ ይተማሉ። የተስፋውን ምልክት የማይሸነፈውን፣ በግርማው ጠላት የሚያስጨንቀውን፣ ኃያልነቱ የማይቻለውን፣ ሚስጥሩ የማይመረመረውን፣ ክብሩ ለዘላለም ከፍ ያለውን፣ ፈጣሪ ያከበረውን፣ አብዝቶ የወደደውን ፣ በኃይሉ የጠበቀውን ለምስክር፣ ለክብር፣ ለፍቅር ያስቀመጠውን ሠንደቅ ከፊት አስቀድመው ይጓዛሉ። አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሠንደቅ ከፊት ቀድሞ፣ ማን ሊገኝ ቆሞ፣ ጠላት ገና በአሻገር ሲያየው ይሸበራል፣ ይደነብራል፣ ወኔው ይክደዋል፣ ጉልበቱ ይደክማል። ኮርቶ መኖር፣ አሸንፎ ማደር፣ በጀግንነት መከበር፣ በኅብረት መዘመር መለያቸው ነው። ለክብርና ለሀገር ሲሉ ዱር ቤታቸው፣ ዋሻ ማደሪያቸው፣ ደርቅ ኮቸሮ ምግባቸው ሆኖ ይኖራሉ። ሀገር ስትወረር፣ ክብር ሲደፈር፣ ቆሞ ማዬት አይቻላቸውም። ዝም ማለት አይሆንላቸውም። ቁጣቸው ይገነፍላል፣ ሳንጃቸው ይሳላል፣ አፈሙዛቸው ይወለወላል። ሀገር የደፈረውን ክብር የነካውን አሳምረው ይቀጡታል፣ ክንዳቸውን ያሳዩታል። አባት ያወረሰው፣ ጀግና የሚወርሰው፣ ቆራጥ የሚለብሰው፣ ፈሪ የማይደርሰው፣ ለዘላለም የሚታጠቁት፣ ካጠለቁ የማያወልቁት ደምና ማንነት ነው ፋኖነት። ፋኖነት አሸናፊነት፣ አይበገሬነት፣ ለሀገር ኗሪነት፣ እምቢ ለነፃነት፣ እምቢ ለሉዓላዊነት ማለት ነው። የአማራ ፋኖ በዘመናት ቅብብሎሽ ሀገር ስትደፈር፣ ግዛቷ ሲወረር እምብኝ እያለ እየተነሳ ደምና አጥንት እየገበረ፣ በጀግኖች ጎራ ውሎ እያደረ ጠላትን መትቷል፣ ራሱ ኮርቶ ሀገር አኩርቷል። በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን የመጣው ሁሉ ለእርሱ ጠላቱ ነው፣ የሚከፍለው ደምና አጥንት ለነፃነት፣ ለሉዓላዊነት፣ ለኢትዮጵያዊነት ነው። የአባቱን ስም የወረሰው፣ ያባቱን ጋሻ ያነሳው ፋኖ ስሙን ሊዘክር፣ ታሪኩን ሊመሰክር፣ ሀገር ሊያስከብር በረሃ ገብቷል። ጠላቱን ሳይቀጣ፣ ከበረሃው አይወጣም። <> ፋኖ ቃሉን ጠብቆ፣ ሡሪውን አጥብቆ ጠላትን መውቃት ይችልበታል። ቃሉን አይሽርም፣ ክንዱን አያዝልም፣ እንደተከበረ እንደ አከበረ ይኖራል እንጂ። የትግራይ ወራሪ ሀገር ሊያፈርስ፣ ቀዬ ሊያረክስ በመጣበት ሁሉ ፋኖው እያደነ እየወቃው ነው። በማይጠብሪ ግንባር የተሠማራው ፋኖ በዱር በገደል እየተከታተለ ወራሪውን ኃይል እየደመሰሰው ነው። እነ አጅሮችን በግንባር አግኝቻቸዋለሁ። ጦር እየመሩ ሀገር ሊያስከብሩ ዘምተው። ጣላት ሳይደመሰስ ከበረሃ ላይመለሱ ምለው። በግንባር ያገኘናቸው የፋኖ ሻለቃ መሪ ስጦታው ዳኘው (ባሻ) ፋኖ በየትኛውም ውጊያ ላይ አለበት፣ በውጊያ ተቋዳሽ ነው ብለውናል። ጎንደርን እንዲቆጣጠር የተላከውን የአሸባሪ ቡድን ጨርሰን የቀረውን ለመደምሰስ በመገስገስ ላይ ነን፣ ፋኖ ተሰማራ ሲባል ጠላት ይሸበራል፣ የአሸባሪው ቡድን የፋኖን ስም ሲሰማ ገና ይሮጣል ነው ያሉን ባሻ። <> ነውም ብለውናል። ፋኖ የአማራ ብቻ አይደለም የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊያን ነው፣ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ፅናት የሚዋደቅ መሆኑንም ባሻ ተናግረዋል። <> ነው ያሉን። ትግራይ አንድ የኢትዮጵያ አካል የሆነች በሃይማኖት፣ በሰውነት አንድ አካል አንድ አምሳል ነን፣ ትግላችን ሀገራችን ሊያፈርሱ ከተነሱና ሀገራችን ለውጭ ወራሪ አሳልፈው ሊሰጡ ከሚጥሩት ጋር ነውም ብለውናል። የፋኖው ትግል መላ ኢትዮጵያውያንን ነፃ ለማውጣት ስለመሆኑም ነው የነገሩን። ወራሪው ኃይል ቄስና መነኩሴ ሳይቀር የሚገድል፣ ሀብትና ንብረት የሚዘርፍ የሚያወድም ነው፣ ለምንም ለማንም የማይጠቅሙ ስለሆኑ እስከመጨረሻው እንታገላቸዋለንም ብለዋል። <> ሲሉም ይገልፁታል። የአማራ ሕዝብ የጀግንነት ታሪክ ይሠራል እንጂ የተዋረደ ታሪክ አይሰራም ነው ያሉት ባሻ። ለኢትዮጵያ እርኩስ መንፈስ የሆነውን ኃይል ከገባበት ገብቶ ያስወጠዋል፣ ጠላት በሽሽት ገድል እየገባ፣ ውኃ እየበላው ነው ሲሉም የጠላትን ሩጫ ባሻ ነግረውናል። የፋኖ የብርጌድ አዛዥ ዮሃንስ ንጉሡ ፋኖ ሀገርና ሕዝብ የሚጠበቅበት አባቶቻችን ያወረሱን ጥንታዊ ተቋም ነው ብለዋል። ውድ ዋጋ እየከፈለ ትልልቅ ድሎችን እያመጣ እየተጓዘ ነው፣ በዘመናዊ አደረጃጀት ተደራጅቶ ሰፊ ቁጥር ያለው ሠራዊት ይዞ በድል እየገሰገሰ ነው ብለውናል። ፋኖ ድል በድል እየሆነ እየማረከ፣ እያንበረከከ፣ እየደመሰሰ መሆኑንም ተናግረዋል። ጠላት አሉኝ የሚላቸውን ጦሮችን አሰልፎ ተዋግቷል፣ ነገር ግን አለኝ የሚላቸውን አጥቷል፣ መቋቋም አቅቶት ወደ ቆላ ተንቤን እየፈረጠጠ ነው ብለዋል። ፋኖ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ ጋር የሚለዬን ነገር የለም፣ በአንድ ምሽግ አድረናል፣ በአንድ ኮዳ ጠጥተናል፣ በአንድነት ለአንድ ዓላማ እየተዋጋን ነው ብለዋል። በግዳጅ ውስጥ ምንም አይነት ሚና የሌላቸው ሰዎች ፋኖ በመምሰል የሚንቀሳቀሱ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ጠይቀዋል። ፋኖ ሲያጠፋም በሕግ እንዲጠየቅ ኾኖ መደራጀቱንም አንስተዋል። ሌላኛው የፋኖ መሪ አርበኛ ደረጀ በላይ(አባ ናደው) ትግሉ የተሳካ እንዲሆን እያገዘ ላለው ሕዝብ ምስጋና ይድረሰው ነው ያሉት፣ ፋኖ ከቀደሙት አባቶች የሚሰመውን ታሪክ እየደገመና እያስመሰከረ ስለመሆኑ ነግረውናል። በመካከላቸው ምንም አይነት ልዩነት አለመኖሩንም ገልፀዋል። ፋኖ የአማራ ሞተር ነው ያሉት አርበኛው የፋኖ አደረጃጀት ሊገደብ አይገባም ብለዋል። የአማራ ሕዝብ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን፣ ልዩ ኃይሉን ከመቀላቀል በላፈ ፋኖን እየተቀላቀለ ሀገሩን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል። ሌላው የፋኖ መሪ የሺህ አለቃ ባየ ቀናው ፋኖ ከጠላት እየማረከ እየታጠቀ በድል እየገሰገሰ ነው፣ በጀታችን እና ደጀናችን ሕዝባችን ነው ብለዋል። ጠላትን እስከመጨረሻው መምታት አደራችን ነው፣ ብዙ ድል አግኝተናል፣ የመጨረሻችን ግን አይደለም፣ ጠላት እንዳያንሰራራ አድርገን መምታት አለብን ነው ያሉት። <> እንደተባለ ከፋኖ ፊት ሲደርሱ ፈሪ ካልሆኑ መጨረሻው ሞት ነው። ጥይታቸው አይምርም፣ አፈሙዛቸው አይስትም። ጀግንነታቸው የሚታይ ነው፣ ምሽግ ሰብረው እንደ አሞራ በረው ከጠላት አናት ላይ የሚሰቀሉ ድንቆች ናቸው። አሚኮ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply