ፋኖ የአለፋ ፖሊስ ጣቢያን ጨምሮ መላ የወረዳ ተቋማትን መቆጣጠሩን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ነሃሴ 2/2015_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአለፋ ወረዳ ዋና ከተማ ሻሁራ ነሃሴ 1/2015 ከቀኑ 12 ሰዓት ገደማ ሻለቃ መላክ ስሜነህ በሚመራው የቴዎድሮስ ብርጌድ እና በአለፋ ፋኖ መያዟ ይታወቃል። የአለፋ ወረዳ የጸጥታ አካላት እኛ ከፋኖ ጋር መዋጋት አንፈልግም በሚል ተቋማትን ለፋኖ እና ለህዝብ እያስረከቡ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ነገር ግን በሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት “እኛ ድንበር ልንጠብቅ ነው የመጣን” በሚል እየተነጋገሩ መሆኑ ተሰምቷል። ይህን ተከትሎም ነሃሴ 2/2015 ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ያለምንም የተኩስ ልውውጥ የአለፋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያን በመቆጣጠር ርክክብ እየተደረገ መሆኑ ተገልጧል። ስለዚህ ማንኛውም ማህበረሰባችን በየጊዜው እየተፈጸመብን ያሉ ድርጊቶችን በተመለከተ መሬት የነካውን እውነታ በማድረስ የመረጃ ልውውጥ እንድታደርጉልን እናሳስባለን። ሰላም ለሕዝባችና ለሀገራችን። ኮሚቴው
Source: Link to the Post