You are currently viewing “ፋኖ ጠላቶቻችን እንደሚሉት ሀገር አፍራሽ እና ጸጥታ አደፍራሽ ሳይሆን ሀገርና ሕዝብ ጠባቂ ስለሆነ የብልፅግናው መንግስት በፋኖ ላይ የሚያካሂደውን ማሳደድ በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን።…

“ፋኖ ጠላቶቻችን እንደሚሉት ሀገር አፍራሽ እና ጸጥታ አደፍራሽ ሳይሆን ሀገርና ሕዝብ ጠባቂ ስለሆነ የብልፅግናው መንግስት በፋኖ ላይ የሚያካሂደውን ማሳደድ በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን።…

“ፋኖ ጠላቶቻችን እንደሚሉት ሀገር አፍራሽ እና ጸጥታ አደፍራሽ ሳይሆን ሀገርና ሕዝብ ጠባቂ ስለሆነ የብልፅግናው መንግስት በፋኖ ላይ የሚያካሂደውን ማሳደድ በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን።” የአማራ ግብረ ኃይል፣ አማራ ማህበር በዩኬ እና ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ግብረ ኃይል፣ አማራ ማህበር በዩኬ እና ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት በጋራ የተሰጠ የአቋም መግለጫ:_ በ21ኛ ክፍለ ዘመን አለም በዘመነበት መንግሥት አለ በሚባልበት አገር ውስጥ የአማራ ህዝብ በገጀራ የሚታረድበት፣ ቤት ተዘግቶ ከህፃን እስከ አዛውንት በሚቃጠልበት እና በአጋጣሚ ከዚህ ሁሉ ሰቆቃ የተረፈው አማራ የትም እንዳይንቀሳቀስ መንገድ ተዘግቶ በምግብ እጦትና በውኃ ጥም በስቃይ ይህችን የጉደኞች አገር የመጨረሻ እንባውን አንብቶ አገሩን ረግሞ ይሰናበታል። ታዲያ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ፖለቲካውንም ሆነ መዝናናትን የማያውቀው ምስኪኑ ገበሬ ይህን ሁሉ ሰቆቃ ሲደርስበት ዝምታው እስከ መቼ? አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ የአማራ ሕዝብ በጠላት ተወሮ ህልውናው አደጋ ላይ በወደቀበት ወቅት ብአዴን የክተት ጥሪ ሲያውጅ ከአቻ ፋኖዎች ጋር በመሆን ሕዝባዊ ኃይል-ፋኖን ያደራጀ እና መስዋዕትነትን የከፈለ የቁርጥ ቀን ልጅ እንጅ ዛሬ “የእናት ጡት ነካሾች እንደገለፁት” አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ ያደራጀው ህግ ወጥ ቡድን አይደለም። አማራ ይታገሳል፤ አሻግሮ ይመለከታል እንጅ በቃ ካለ ያበቃል። ሁልግዜም የአማራው ፈተና አማኝ እና ታማኝነቱ ነውና በቅርቡ ወንድማችን አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ በሽምግልና ስም በብአዴን የተፈፀመበት ክህደት የነበረችንን የተስፋ ቀጭን ክር በጥሷታል። በአርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴና ባልደረቦቹ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ክህደት እና እስር በጽኑ እያወገዘን፣ መላው የአማራ ሕዝብ ፋኖዎቹን ነጻ የማውጣትና ብሎም ነጻነቱን ማረጋገጫ ሁሉን አቀፍ ትግል አጠንክሮ እንዲያቀጣጥል ጥሪያችንን እያቀረብን፣ ብአዴን አማራን አሳልፎ እንደሸጠ ዋና ማሳያው ክልሉን እየመራ ያለው የኦሆዲድ-ኦሮሙማው ክንፍ ስለሆነ በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ እንዲሁም አርበኛ ዘመነ ካሴ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንጠይቃለን። 1) አማራ ክልል የገባው የኦነግ ሠራዊት፣ የመከላከያ እና የአማራ ልዩ ኃይልን ልብስ በመልበስ ተመሳስለው የመከፋፈል ሴራ ሲሰሩ ስለቆዩ አማራ የእርስ በእርስ የመጠፋፋት ወጥመድ ውስጥ ሳትገባ በብልሃት እንድትሻገር፣ የአብይ አህመድ መንግሥትና የብአዴን አሻንጉሊቶች በጋራ የሚሰሩት አማራን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት በመንግሥት ድጋፍ እና አመራር በወለጋ፣በመተከል፣ በወሎ፣በሸዋ፣በጎንደር ሰው መርጦ ባልተፈጠረበት ማንነት እና በውሸት ትርክት የአማራን ማህበረሰብ ከነህይወቱ እየተቃጠለ እና እየታረደ ዘር ማጥፋት ሲፈፀምበት እንዲሁም የአማራ ተማሪዎችን ማስገደል እና ማፈናቀል ህጋዊ ያደረገውን የአብይ አህመድ መንግሥት ተጠያቂ እንዲሆን እንጠይቃለን። 2) አማራ መዳኛው ጠላቶቹን አውቆ በአንድነት መቆምና እንደ ሁልጊዜው ሁሉ በእራሱ እና በእግዚያብሄር በመተማመን ብቻ የመላው አማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ትግሉን ማጠናከርና ፋኖነት ታላቁ እሴቱን አስጠብቆ፣ ለዘመናት ህልውናውን እና የአገሩን ዳር ድንበር አስጠብቆ የኖረ ታላቅ ህዝብ መሆኑን በመገንዘብ፣ የዛሬዎቹ የዘመናችን ተላላኪዎች የአማራ ህዝብ ትውልድ ዘለል እሴት የሆነውን “ፋኖነት” ኢ-መደበኛ ብሎ ወገኖቻችንን ማሳደድ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን። 3) የኦሮሞ አስተዳደር በፌደራል በጀት በተሟላ ሎጂስቲክ 48 ዙር በዳቦ ስሙ“ኦነግ ሸኔ” የተባለውን አሸባሪ አሰልጥኖ አማራን እያሳደደ፣እያረደ እና ንብረት እያወደመ የአማራ ማህበረሰብንና አገራችንን በ60 ዓመት ወደ ኋላ የመለሰ፣ ኦነግና ትህነግ በጋራ በብልፅግና ተብዬው ፈቃድና እገዛ አገርን እያሸበሩ ባሉበት ወቅት ፋኖን ፣ የአማራ ሚሊሻንና ልዩ ሃይላችንን ከኋላ በማስመታት፣ ማሰርና ማሳደድ የብአዴን ክህደት ከእይታ ውጭ ስላልሆነ ህዝቡ ነቅቶ በመጠበቅ በጋራ እንዲያከሽፈው እና ለኦሮሙማ መስፋፋት ሲባል የሚከፈለው መስዋዕትነት አጥብቀን እያወገዝን፣ የአማራ እልቂት በወለጋ፣ በመተከል፣በጉራ-ፈርዳ ዛሬም የቀጠለው የአማራን ዘር የማጥፋት ጭፍጨፋ እንዲቆም እና ለተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የጠ/ሚ አብይ አህመድ መንግሥት ሙሉ ሃላፊነቱን እንዲወስድ እንጠይቃለን። 4) አገራችን ኢትዮጵያን ወደ ሰላም መንገድ እንድትገባ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ያለውን ፋኖ ትጥቅ ለማስፈታት እየተንቀሳቀሰ ያለውን የብአዴን ስብስብ በአስቸኳይ እንዲያቆም; የመላው አማራ ህዝብ እንዲቃወመውና ፋኖን እንዲቀላቀል የእራሱንና የቤተሰቡን ደህንነት እንዲያስጠብቅ እያሳሰብን; የአማራ መሪ ነን በሚሉ ደመቀ መኮንን፣ አገኘው ተሻገር፣ ይልቃል ከፍያለው፣ ግርማ የሺጥላ፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ አብርሃም አለኸኝ፣ አብርሃም አያሌው፣ሰማ ጥሩነህ፣ኮሚሽነር ክንዱ፣ብናልፍ አንዷለምና መሰል የብአዴን ካድሬ እና ደንገጡሮች ይህንን ጀግና ህዝብ ተዋርደው ያዋረዱትን ከራሱ ላይ አውርዶ መጣልና የህልውና ዘመቻውን መቀላቀል ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው፤ ጀግና ህዝብ በአሳማ ተመርቶ አሸናፊ ሊሆን አይችልም እና ዘላቂ መሪህን እንድትመርጥ እናሳስባለን። 5) በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ሃይ ባይ ያጣውን ዘር የማጥፋት ጭፍጨፋ እና ከቦታ ቦታ አዲስ አበባና ጨምሮ እንዳትንቀሳቀስ በወራሪው ኦሮሙማው መንግስት ስትታገድ እና ቅርስህን ሲያጠፉና ንብረትህን ሲያወድሙ በቃ የምትልበት ጊዜ ነገ ሳይሆን ዛሬ በጋራ ተነስተን ለማስቆም ያለንን አቅም ሁሉ አስተባብረን የምንሰራበት የመጨረሻዋ ሰዓት ላይ ስለምንገኝ ሁሉም አማራ እና ሰው የሆነ ሁሉ በአንድነት ኃይሉን በማስተባበር ትግሉን መቀላቀል ጊዜው የሚጠይቀው የህልውና ዘመቻውን ግዴታ ነው። ፋኖ ጠላቶቻችን እንደሚሉት ሀገር አፍራሽ እና ጸጥታ አደፍራሽ ሳይሆን ሀገርና ሕዝብ ጠባቂ ስለሆነ የብልፅግናው መንግስት በፋኖ ላይ የሚያካሂደውን ማሳደድ በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን። 6) መላው የአማራ ሕዝብ በፋኖወች ላይ የሚደርሰውን በመንግሥት ካድሬዎች የተቀነባበረ የማዋከብና የማጥፋት ዘመቻ ለማስቆም በመንግስት ላይ አስፈላጊዉን ጫና በማድረግ ከፋኖ ጎን እንድትቆሙ ፣ በመንግሥታዊ መዋቅር ተደራጅቶ የመጣውን አገር በቀል ጠላት ለመመከት ሁሉም አማራ የህልውና ዘመቻውን እንደ አቅሙና ችሎታው ለማገዝ መቀላቀል የመኖር አለመኖር ግዴታ እንደሆነ አጥብቀን እናሳስባለን። 7) አማራ መሆን ወንጀል የሆነበት አገረ ኢትዮጵያ: በሙያቸው አገራቸውንና ወገናቸውን ለማገልገል በጥቅም ተገዝተው ሳይሆን እውነታን በመገንዘብ የአገርን ሰላምና አንድነት ሊያመጣና የህግን የበላይነት ለማስጠበቅ መረጃን ከቦታው በማድረስና በመዘገብ የሚታወቁ ጋዜጠኞችን ፣ ህግና ደንብን አክብረው የሚሰሩ ፖለቲከኞች ፣ ሙህራኖች ፣ ፀጥታ አስከባሪዎች ፣ እንዲሁም አክቲቪስቶችን እንደ መዓዛ መሃመድ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ አሳዬ ደርቤ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣ ቢኒያም ታደሰ እና ሌሎችም ከእውነት ጋር የተጣላው የዘረኛውና የተረኛው ኦሮሙማው መንግስት ተብዬ ማመን በሚከብድ ሁኔታ አራጆቹን እየተንከባከበ፣ ንፁሃን ዜጎችን ማንገላታት ማሰርና ማዋከብ እንዲቆምና የታሰሩት በአስቸኳይ እንዲፈቱም እንጠይቃለን። 8) የኦሮሙማው ቅጥረኛ አገልጋዩ ብአዴን ታማኝነቱን ለጌታው ለማረጋገጥ የአማራን ማህበረሰብ በማዳከም ብሎም ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የሚሰራው ሴራ እራሳቸውን ሊከላከሉ ብሎም የአገራቸውን ዳር ድንበር ሊያስጠብቁ ይችላሉ የተባሉትን የአማራ ልዩ ኃይል፣ሚኒሻ እና ፋኖን ማስገደል፣ ማሳደድ፣ ማሰር እንዲቆምና ብሎም ወንጀላቸው አማራ መሆናቸው ብቻ ያሳሰራቸው ከ5ወር በላይ የተሟላ ምግብ፣ መጠጥና ህክምና ሳይቀርብላቸው በአገዛዙ ትዕዛዝ በቅጥረኞች ተገለዋል፤ ተደብድበዋል እንዲሁም የተበላሸ ምግብና ውሃ በመስጠት ብዙዎች ታመዋል፣ በየቀኑ ሕይወታቸው ያልፋል። ለጊዜው ከሞት የተረፉት ከ20,000 በላይ ቁጥር ያለው የአማራ ወጣት በባከር ፣ በአፋር በረሃ እና በተለያዩ ቦታዎች ላይ ወድቀው የሲቃ ድምፃቸውን እያሰሙ ላሉት ወገኖቻችን እንድረስ እንዲሁም በሰኔ 15 በአማራ ክልል መሪዎች ግድያ ተጠርጥረው የጦስ ዶሮ የተደረጉት ታሣሪ የአማራ ንፁሃን የቁርጥ ቀን ልጆች, “ወንጀለኞቹ በነፃነት አራት ኪሎ ስለሚገኙ” ንፁሃን ዜጎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን። 9) የትግራዩ አሸባሪው ትህነግ በ2013ዓ.ም. በመከላከያ ነባር ሠራዊቶቻችን ላይ የፈፀመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ በተቀነባበረ አካሄድ ከፌደራሉ መንግሥት ጋር በተቀናጀ አማራ ተወላጆች ላይ የተፈፀመው መቼም የማይረሳ ሲሆን፣ በወለጋ ሆሮ-ጉድሩ አማራዎችን ት/ቤት አዳራሽ ውስጥ ለስብሰባ ጠርቶ ከ300 ሰዎች በላይ የኦሆዲድ ብልፅግና ተወካይ በተገኘበት በከባድ መሣሪያ በፈጃቸው በ6ኛው ቀን በትግራይ በመከላከያው ውስጥ ለ20 አመት አብረዋቸው የቆዩትን አማራ በመሆናቸው ብቻ አገር ደህና ብለው በተኙበት ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተፈፅሞባቸዋል። ዛሬም ወራሪውን አንድ ክልልን በፌደራል ደረጃ ማስቆም፣ ማጥፋት ወይም ማሸነፍ አቅቶት ሳይሆን ስልጣንን ለማቆየትና አማራን የመጨረስ እንዲሁም ክልሉን አድቅቆና አዳክሞ የመሰልቀጥ ሴራ ስለሆነ ህዝብን ሰላም በመንሳት የትህነግ ወረራን ለ3ኛ ጊዜ ለመመከት በተባለ ትርክት ንፁሃኑ ሕዝብ ያልቃል። ለእርዳታ የገባው ስንዴ ማዳበሪያ ተቀይሮለት ኦሮሚያ አመረተች በሚል ቅዠት ውስጥ የገባው የአብይ አህመድ መንግሥት ወደ ጎረቤት አገር እየላከ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን በቀን አንድ ዳቦ መቅመስ ከአቅሙ በላይ ሆኖበት በችግር ውስጥ ይገኛል። ስለዚህ የአገራችን ህዝብ ሆይ አስተውል ወደ ህሊናህ ተመለስና እየተሰራብህ ያለውን ደባ በመገንዘብ ህልመኛ እና አወናባጅ መንግሥት ተብዬ ሥልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ አቅምህን እንድታሳይ እናሳስባለን። 10) አገር ወዳዱ የአማራ ህዝብ ሆይ እስከ ዛሬ እየሞትህ ፣እየቆሰልህ፣ እየታሰርህ፣እየተደበደብህ አገሬ እንዳትፈርስ በማለት የሞተውን አልቅሰህ ቀብረህ ተሰናብተኸዋል። ዛሬ ግን ለወገኖችህ ሁለት ሜትር የክብር ቀብር ተከልክለህ ወገን በእሳት ወደ አመድነት እየተቀየረ እንደሆነ ተገንዝበናል። ወንጀለኛው መንግሥት በፈጠረው ጦርነት የተሰለፈው የሰለጠነ ፋኖን ከፊትና ከኋላ በአሻጥር ማስመታት፣ በብዙ ውጣ ውረድ እራሳቸውን አደራጅተውና አሰልጥነው የተዘጋጁትን የአማራ ፋኖ በማሳደድና ትጥቅ በማስፈታት ፣ ሕዝቡን ለተስፋፊው ኦሮሙማ ኃይል ምቹ ሜዳ ለመፍጠር ሲባል ከ20,000 በላይ በተለያዩ ቦታዎች በማሰር በምግብ እጦትና በበሽታ መጨረስ፣ መከላከያ ውስጥ የገባውን አማርኛ ተናጋሪ ወደ ኦሮሞ ክልል በመላክ በአሻጥር ማሳረድ ፣ አሁን ደግሞ ከአማራ ክልል በብአዴን ካድሬዎች የሚመራው የአማራን ወጣት ማስጨረሻ ዘዴ፣ 300,000 አዲስ ሰልጣኝ ወደ መከላከያ እንዲገባ እያስገደዱ ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ዘርፈ ብዙ ተንኮላቸውን በማክሸፍ የጥፋት ህልማቸውን እንድታመክን፣ ሸረኞችንና በአንተ ህይወት የሚቆምሩትን በቃ ለማለት የህልውና ትግሉን በመቀላቀል እራስህንና ቤተሰብህን እንዲሁም አገርህን ከአፍራሾች ነፃ እንድታወጣ ጥሪ እናደርጋለን። አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል! ድል ለሰፊው ህዝብ አማራ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply