ፌስቡክ መቀመጫቸዉን በዉጭ አድርገዉ ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠሩ አካዉንቶችን መዝጋቱን ገለጸ፡፡አካዉንቶቹ መቀመጫቸዉን ከግብጽ ማድረጋቸዉን የገለጸዉ ፌስቡክ፣ ራሳቸውን ለማስተዋወቅ እስከ 525 ሺ…

ፌስቡክ መቀመጫቸዉን በዉጭ አድርገዉ ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠሩ አካዉንቶችን መዝጋቱን ገለጸ፡፡

አካዉንቶቹ መቀመጫቸዉን ከግብጽ ማድረጋቸዉን የገለጸዉ ፌስቡክ፣ ራሳቸውን ለማስተዋወቅ እስከ 525 ሺህ ዶላር ወይም በወቅታዊ የምንዛሬ ዋጋ 21 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ማውጣታቸውን ይፋ አድርጓል።

ኩባንያዉ እንዳለዉ እነዚህ አካዉንቶች ያስቀመጥኩትን በዉጭ ሀገራት ጣልቃ አለመግባት የሚለዉ ህግን ተላልፈዉ አግኝቻቸዋለሁ ነዉ ያለዉ፡፡

በዚህ ምክንያትም መዘጋታቸዉን ነዉ የገለጸዉ፡፡

በግብጽ መቀመጫቸውን አድርገው ኢትዮጵያ ላሉ ተከታዮች መልዕክት ከሚያስተላልፉ ገፆች ዉስጥም በኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ትችት የሚያቀርቡና የተሳሳተ መረጃ የሚለቁ ይገኙበታል ብሏል፡፡

አካዉንቶቹ በእዉነተኛ ስምና በአሳሳች ማንነት ጭምር የተከፈቱ መሆናቸዉንና በየጊዜዉም እንደሚለዋወጡ ነዉ የገለጸዉ፡፡

ፌስቡክ ያገዳቸዉ ገጾችም ከ300 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሏቸዉ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

ቢቢሲ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply