“ፌሽታ” የተሰኘ የሕፃናትና የወጣቶች ፌስቲቫል በቀጣይ ሳምንት ሊካሄድ ነው

አርብ ታህሳስ 5 ቀን 2016(አዲሰ ማለዳ) የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ፌሽታ የተሰኘ የሕፃናትና ወጣቶች ፌስቲቫል በመጪው ታህሳስ 13 እና 14 ቀን 2016 በኤቫ ሌግዠሪ ሰርፕራይዝ ፕላነር አዘጋጅነት ሊካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

በጊዮን ሆቴል በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል ላይ ከ5 ሺሕ በላይ ህጻናት ይገኙበታልም ነው የተባለው።

በመርሐግብሩ ላይ የሕፃናት እና ወጣቶች ዕቃ አስመጪና አቅራቢዎች ፣ የስጦታ ዕቃ አስመጪና ሻጮች፣ ምግብና መጠጥ አቅራቢዎች ፣ የመዝናኛ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ተቋማት በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

በዕለቱ መግቢያው 250 ብር ሲሆን ቲኬቱን ከነገ ታህሳስ 6 2016 ጀምሮ በቴሌብር ላይ እንደሚሸጥ ተገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply