You are currently viewing ፌደራል ፖሊስ በአማራ ክልል የዞን እና የወረዳ ጤና መምሪያዎችን በማስገደድ ሀሰተኛ የሞት ሪፖርት መቀበሉ ተሰማ‼ ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ፌደራል ፖሊስ በእነ ዶ/ር ወንድ…

ፌደራል ፖሊስ በአማራ ክልል የዞን እና የወረዳ ጤና መምሪያዎችን በማስገደድ ሀሰተኛ የሞት ሪፖርት መቀበሉ ተሰማ‼ ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ፌደራል ፖሊስ በእነ ዶ/ር ወንድ…

ፌደራል ፖሊስ በአማራ ክልል የዞን እና የወረዳ ጤና መምሪያዎችን በማስገደድ ሀሰተኛ የሞት ሪፖርት መቀበሉ ተሰማ‼ ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ፌደራል ፖሊስ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ክስ የመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች በአማራ ክልል በቀሰቀሱት አመፅ በርካታ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል በሚል በክልሉ የዞን እና የወረዳ ጤና መምሪያዎችን በማስገደድ ሀሰተኛ የሞት ሪፖርት መቀበሉን የአማራ ድምፅ ካሰባሰበው መረጃ ለማረጋገጥ ችሏል። በአማራ ክልል በሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች የተሰማራው የፌደራል ፖሊስ ቡድን “ምን ጠፋባችሁ? ምን ያህልስ ከሰራችሁ?” በሚል የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ሀሰተኛ ሪፖርት እንዲፅፉለት ያስገደደ ሲሆን ይህንን ሀሰተኛ ሪፖርትም ተጠርጣሪዎቹ በቀሰቀሱት አመፅ የጠፋ የሰው ህይወትና ንብረት በሚል በክሱ እንዲካተት ተደርጓል። ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተላከው ግበረ ኃይሉ በየዞኑ እና በየወረዳው የሚገኙ ጤና መምሪያዎችን በማስገደድ በህመም እና በተለያዩ ምክኒያቶች በየሆስፒታሉና በየጤና ጣቢያው ህይወታቸው ያለፈን ሰዎች ጭምር በማካተት ሀሰተኛ የሞት ሪፖርት እንዲፃፍለት ያስደረገ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ በቀሰቀሱት አመፅ የተገደሉ ሰዎች ዝርዝር በሚል የክሱ አንድ አካል መሆኑ ታውቋል። በርካታ የዞንና የወረዳ ጤና መምሪያዎች ተጠርጣሪዎቹ ቀሰቀሱት በተባለው አመፅ ህይወቱ ያለፈ ሰው እስከ አሁን በተቋማችን አላጋጠመንም የሚል ምላሽ የሰጡ ቢሆንም ነገር ግን ከአመፁ ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ መፃፍ እንዳለባቸው ነው ማስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ የተሰጣቸው ተብሏል። ስለሆነም የጤና መምሪያዎቹ በዚህ ሁለት ወራት በየተቋሞቻቸው በተለያየ ምክኒያት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎችን ዝርዝር ከአመፁ ጋር በማያያዝ ለግብረ ኃይሉ ተገደው ሪፖርት ማድረጋቸውን ነው ለደህንነታቸው ሲባል የእሳቸው እና የተቋማቸው ስም ያልተጠቀሰ የአይን እማኝ ለአማራ ድምፅ የገለፁት። አንዳንድ ጤና መምሪያዎች በወሊድ ምክኒያት ህይወታቸው ያለፈ እናቶችን እና በመኪና አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ስም ዝርዝር ከአመፁ ጋር አያይዘው ሪፖርት አድርገዋል ተብሏል። አንዳንዶች ደግሞ ኤች አይ ቪ ኤድስን ጨምሮ በተለያዩ በሽታወች ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ስም ዝርዝር በተቀሰቀሰው አመፅ ህይወታቸው ያለፉ ናቸው በሚል በተሰጣቸው አስገዳጅ ትዕዛዝ መሠረት ለግብረ ኃይሉ ደብዳቤ ፅፈዋል ሲሉ የአይን እማኛችን ገልፀዋል። በባህርዳር ከተማ የሚገኝ አንድ ትልቅ ሆስፒታል ተቀሰቀሰ በምትሉት አመፅ ምክኒያት ህይወቱ ያለፈም ሆነ ጉዳት ደርሶበት ወደ ተቋማችን የመጣ ሰው የለም በሚል ለግብረ ኃይሉ ምላሽ በመስጠቱ በአስተዳደር አካላቱ ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ ተፈፅሟል ሲሉ ሌላኛው የአማራ ድምፅ የመረጃ ምንጭ ተናግረዋል። ተጠርጣሪዎቹ በቀሰቀሱት አመፅ በርካታ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል በሚል ከፍተኛ የሟች ቁጥር ለግብረ ኃይሉ ሪፖርት ካደረጉት መካከል በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጤና መምሪያ አንዱ መሆኑንም ምንጮቻችን ጠቁመዋል። ፌደራል ፖሊስ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን መዝገብ የተካተቱ 51 ተጠርጣሪዎች ቀስቅሰውታል ባለው አመፅ ህይወታቸው አልፏል በሚል ከተቀበለው የሟቾች ዝርዝር ሪፖርት በተጨማሪ በክልሉ በሚሊየኖች ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል በሚል በየአከባቢው አስገዳጅ ሀሰተኛ ሪፖርት ማስፃፉም ነው የተገለፀው። በየወረዳው እና በየዞኑ የሚገኙ ተቋማት በአመፅ ምክኒያት የወደመብን፣ የከሰርነው ንብረት የለም ያሉ ቢሆንም ነገር ግን ከሁለት ወራት ወዲህ በተለያዩ አጋጣሚወች የጠፋ ንብረት ካላቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ ግብረ ኃይሉ አስገዳጅ መመሪያ ሰቷል ሲሉ በሰሜን ወሎ ዞን በመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰሩ አንድ ባለሞያ ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል። ግብረ ኃይሉ ዞንና ወረዳዎች በተለያየ ምክኒያት የጠፋባቸውን ንብረት በዝርዝር እንዲገልፁለት በሰጠው አስገዳጅ ትዕዛዝ መሠረት አንድ ወረዳ ለቢሮ ፅዳት አገልግሎት የተቀመጠ አራት ፈሳሽ ሳሙና ጠፍቶብኛል በሚል ሪፖርት ያደረገ ሲሆን፡ ይህም ተቀሰቀሰ በተባለው አመፅ የጠፋ ንብረት በሚል በክሱ ውስጥ ተካቷል ነው የተባለው። ሌላኛው በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኝ አንድ ወረዳ ደግሞ ለስራ የምንጠቀምበት አንድ ተሽከርካሪ የኋላ ፍሬቻ ባልታወቀ ሁኔታ ተሰብሮብናል የሚል ሪፖርት ለግብረ ሀይሉ ያቀረበ ሲሆን ይህም በአመፁ የወደመ ንብረት በሚል በክሱ ላይ እንዲካተት መደረጉ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር በባህር ዳር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በባህርዳር ከተማ በተፈጠረው አመፅ የጠፋባችሁን ሀብትና ንብረት እንዲሁም አመፁ ባይፈጠር ኖሮ ልታገኙት የምትችሉትን ገንዘብ አስልታችሁ አሳውቁኝ የሚል አስገዳጅ ትዕዛዝ ከግብረ ኃይሉ በተደጋጋሚ የተሰጠው ቢሆንም ነገር ግን መስሪያ ቤቱ ምንም አይነት ሀብትና ንብረት አልጠፋብኝም የሚል ምላሽ በመስጠቱ በአስተዳደር አካላቱ ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደተፈፀመባቸው ለአማራ ድምፅ የደረሰው መረጃ አመላክቷል። ወደ አማራ ክልል የተላከው የፌደራል ፖሊስ ግብረ ኃይል ያስፃፈውን በማስፈራሪያና በማባበያ የተደገፈ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ደረሰ የተባለውን የጉዳት መጠን ሪፖርትን ጨምሮ መርማሪ ፖሊስ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን አሰባስቤ ጨርሻለው በማለት መዝገቡን ለዐቃቢ ህግ ያስተላለፈ ሲሆን ዐቃቢ ህግም በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ መስርቷል። ዐቃቤ ህግ ብዛታቸው 51 የሚሆኑ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ የአማራ ፋኖ አመራሮችና አባላት፣ የጉልበት ሰራተኞችን እንዲሁም ሌሎችንም በአንድ መዝገብ በማካተት ነው 970 ገፅ ማስረጃ አለኝ ያለውን የ71 ገፅ ክስ የመሠረተው። ከእነዚህ መካከል 24ቱ ባሉበት፤ ቀሪዎቹ 27 የሚሆኑት ደግሞ በሌሉበት ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑን ይታወቃል። የአማራ ድምፅ እንደዘገበው “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply