You are currently viewing ፌዴራል ፖሊስ ስንታየሁ ቸኮልን እዚህ ያመጣው የአፋርን ሕዝብ ለማስጠላት ነው———የአፋር ፍርድ ቤት መጋቢት 03 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን…

ፌዴራል ፖሊስ ስንታየሁ ቸኮልን እዚህ ያመጣው የአፋርን ሕዝብ ለማስጠላት ነው———የአፋር ፍርድ ቤት መጋቢት 03 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን…

ፌዴራል ፖሊስ ስንታየሁ ቸኮልን እዚህ ያመጣው የአፋርን ሕዝብ ለማስጠላት ነው———የአፋር ፍርድ ቤት መጋቢት 03 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የምህላና የጥቁር መልበስ ጥሪ ተከትሎ በአዲስ አበባ ጎፋ ገብርኤል በጸሎት ላይ እንዳሉ በግፍ የታሰሩት ፖለቲከኛው አቶ ስንታየሁ ቸኮል (አስጨናቂ) ጉዳያቸውን የመዳኘት ሥልጣን በሌለው ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በአፋር መስተዳድር አዋሽ ሰባት የሚገኘው የፈንታሌ ወረዳ ፍርድ ቤት አቶ ስንታየሁ በሀሰት የተወነጀሉበትን የሽብር ዶሴ የመዳኘት ሥልጣን እንሌለው ቢገልፅም በሕገ ወጥ ሂደት መዝገቡን ገልጦ እንዲዳኝ በኦሮሞ የወረራ አገዛዝ ታዝዟል። ይሁን እንጂ ከሥልጣኑ ውጭ የሆነን ዶሴ መዳኘት እንደማይገባው አሁንም እየገለፀ ይገኛል። የወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት አቶ ሳዲቅ መሀመድ ችሎት ከተሰየሙ በኋላ መርማሪ የፌዴራል ፖሊስን ሲያፋጥጡ ታይተዋል። “እኛ የከፈታችሁትን ምርመራ የመዳኘት ሥልጣን አልተሰጠንም። ሥልጣኑ ያላቸው ፍርድ ቤቶች እዚያው አዲስ አበባ አሉ። ከፈለጋችሁም ከአዲስ አበባ ጎረቤት ደብረ ዘይትና ናዝሬት አሉላችሁ። እነርሱን ረግጣችሁ አልፋችሁ ነው እዚህ የመጣችሁት። አቶ ስንታየሁ ቸኮልን ከአዲስ አበባ እዚህ ያመጣችኋቸው የአፋርን ሕዝብ ለማስጠላት ነው” ብለዋል። አቶ ስንታየሁ ቸኮል በበኩላቸው “ለአፋር ሕዝብ እና ለክልላዊ መንግሥቱ ክብር አለኝ። የፌዴራል መንግሥቱ የበቀል በትር ላይ እጃችሁ እንደሌለበት እተማመናለሁ” ብለዋል። አቶ ስንታየሁ ዳኛው ላቀረቡት ማብራሪያ እና ጥያቄም አመስግነዋል። መረጃው የፅናት ሚዲያ ነው ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply