ፍሬ ከከናፍር (አሻራ ታህሳስ 24፣ 2013 ዓ.ም) “መስጂዱ መመታቱን የሰማሁት የጦርነቱ ሰሞን ነበር..” – ፕሮፌሠር አደም ካሚል… “የአል – ነጃሺ መስጂድ ግንባታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ስራ…

ፍሬ ከከናፍር (አሻራ ታህሳስ 24፣ 2013 ዓ.ም) “መስጂዱ መመታቱን የሰማሁት የጦርነቱ ሰሞን ነበር..” – ፕሮፌሠር አደም ካሚል… “የአል – ነጃሺ መስጂድ ግንባታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ስራ…

ፍሬ ከከናፍር (አሻራ ታህሳስ 24፣ 2013 ዓ.ም) “መስጂዱ መመታቱን የሰማሁት የጦርነቱ ሰሞን ነበር..” – ፕሮፌሠር አደም ካሚል… “የአል – ነጃሺ መስጂድ ግንባታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ስራ ነበር የቀረው። በውቅሮና አካባቢው በነበረው ውጊያ ሰሞን ነበር የአል ነጃሺ መስጂድ መመታቱን የመስጂዱ ግምባታ ኮሜቴ የነገሩኝ። ነገሩን ዋጥ አድርጌ ዝም አልኩ። ጦርነት አውዳሚ ገዳይና አጥፊ ነው። በየመን ሶሪያና ሊቢያም የታየው ይኸው ነው። አልነ-ጃሺን ያህል የአገር ቅርስና ጥልቅ አንድምታ ያለው መስጂድ እንዲህ መሆን ያስደነግጣል፤ ያሳዝናል። መስጂዱ ሆን ብሎ ሊመታ የሚችለው ኢትዮጵያ በአረቡ አለም እንደስጋት እንድትታይ፣ የሐይማኖትን ስስ አጀንዳ ከፖለቲካ ላልዘለለ ትርፍ ለማዋል በተመኙ አኩራፊዎች ነው። በመሆኑም ሙስሊሙም ሆነ መላው ኢትዮጵያዊ ስለ ክስተቱ መነሾና ውጤት ቆም ብለው ሊያስቡ ያሻል። መስጂዱ ታላቅ እስላማዊ ቦታ ብቻ ሳይሆን ታላቅ የቱሪዝም ሐብታችንም ነው። ሁሉም ዜጋ ቅርሱን በባለቤትነት መንፈስ ይመልከተው። መንግስትም ስለ ሁኔታው የሆነ መግለጫ ቢሰጥበት እላለሁ” – ፕሮፌሠር አደም ካሚል ለጋዜጠኛ እስሌማን ዓባይ እንደነገሩት፡፡ https://m.youtube.com/channel/UCsfBw4xrhJzdMTzhWk_uX2A…

Source: Link to the Post

Leave a Reply