ፍርድ ቤቱ ለወንጀሉ መፈጸም የሚያመላክቱ ሰፊ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎቹ በመኖራቸው 12 ተጨማሪ ቀናት ፈቀደ

ፍርድ ቤቱ ለወንጀሉ መፈጸም የሚያመላክቱ ሰፊ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎቹ በመኖራቸው 12 ተጨማሪ ቀናት ፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) እነ ብርጋዴር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዴ (ወዲነጮ) ጨምሮ ሰባት የመከላከያ ከፍተኛ የጦር መኮነኖች ላይ መርማሪ ፖሊስ ባከናወነው በርካታ ማስረጃ ለወንጀሉ መፈጸም የሚያመላክቱ ማስረጃዎች በመኖራቸው 12 ተጨማሪ ቀናትን ፈቀደ፡፡

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በይደር ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተጠርጣሪዎቹን አስቀርቦ መርማሪ ፖሊስ ሰፊ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎቹን መሰብሰቡን ነው የገለጸው፡፡

ስለሆነም ቀሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ሲል ለመርማሪ ፖሊስ 12 ቀናት የፈቀደው ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎች ትናንት ባቀረቡት የስኳር ህመም መመርመሪያ የህክምና መሳሪያ ይግባልኝ ጥያቄ ተቀብሏል፡፡

በዚህም መሰረት መመርመሪያ ኪት እንዲገባላቸው አሊያም በማረፊያ ቤታቸው የህክምና ክትትል እንዲደረግላቸው አዟል፡፡

በተጨማሪም ችሎቱ ትናንት የቀረበው የባንክ ሂሳብ እግድ ይነሳልን ጥያቄያቸውን መርምሮ እግዱን ያገደው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እግዱን ያገደበት ምክንያት አስተያየቱን እንዲያቀርብ አዟል፡፡

በታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል

https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ፍርድ ቤቱ ለወንጀሉ መፈጸም የሚያመላክቱ ሰፊ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎቹ በመኖራቸው 12 ተጨማሪ ቀናት ፈቀደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply