ፍርድ ቤቱ በብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ላይ የ10 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ::ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት ተብሏል፡፡የአማራ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Pj5QmB59r845bomATOXkKfQ0-8tn0sgK1kbad0VonjTrW7l-yo9pQ5gTFILFR1zLUiWaBxIVKyOVvJ08252Z2Vpx0n6R-2e0iWmHZJqL3DR1RXeiEXpim-mVBZ99FDIwy3hsN7NY7YpcM7UbfV4KuoXEhquSb5ZPjkGlGGw7cZcZlUwdXt3MOhB_D5oe5K_nBvn5Q9ccNN7bMKWueOKflkcE0L0GsgGeWyjw9nzZi8t7g-9t9grU33KJ030kKLpr4SPztZi_5Yp3MU1aMyvBHByGNEp8T-2h5yIWnyx9jJDA_VFYFCIYwxcwJfpIOlcX-q8nHeMzYgLUwUm1tjwI7w.jpg

ፍርድ ቤቱ በብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ላይ የ10 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ::

ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት ተብሏል፡፡
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀድሞው የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄ/ል ተፈራ ማሞ ላይ የ10 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።

ዛሬ ጠዋት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብለው የነበሩት ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ዛሬ ከሰዓት መልስ መቅረባቸውን ጠበቃቸው አቶ ሸጋው አለበል ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል።
ህገ መንገስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል በሚል ፍርድ ቤት መቅረባቸውንም ነው ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ለ14 ቀናት ታስረው እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ 10 ቀን ብቻ በመፍቀድ ለግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱንም አቶ ሸጋው ተናግረዋል።

የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄ/ል ተፈራ ማሞ ባሳለፍነው ሰኞ በአዲስ አበባ ባልታወቁ ሰዎች መታፈናቸው መገለጹ ይታወሳል።
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የፌደራል መንግስት ከህወሃት ጋር ባደረገው ጦርነት በፌደራል መንግስት ጦር እዝ ስር በመሆን ውጊያ ሲመሩ፣ ሲዋጉና ሲያዋጉ መቆየታቸው አይዘነጋም።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply