You are currently viewing ፍርድ ቤቱ እነ ጀንበር አብዶ (21) ሰዎች በተከሰሱበት ጉዳይ ብይን ለመስጠት ለሀምሌ 27 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።      አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 29/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ…

ፍርድ ቤቱ እነ ጀንበር አብዶ (21) ሰዎች በተከሰሱበት ጉዳይ ብይን ለመስጠት ለሀምሌ 27 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 29/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ…

ፍርድ ቤቱ እነ ጀንበር አብዶ (21) ሰዎች በተከሰሱበት ጉዳይ ብይን ለመስጠት ለሀምሌ 27 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 29/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለሀምሌ 27 ቀን 2015 ቀጠረ። እነ ጀንበር አብዶ (21) ሰዎች በተከሰሱበት የወንጀል ጉዳይ በቀቀደመ ቀጠሮአቸው መሰረት ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ/ም ፍ/ቤት ቀርበዋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ ማዕከል ቡታጅራ አካባቢ ተዘዋዋሪ ችሎት በተከሰሾች እነ ጀንበር አብዶ (21) ሰዎች በተከሰሱበት የወንጀል ህግ እንቀጽ 238 እና 239 ላይ የተከሳሾች ጠበቆች ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ ፍርድ ቤቱ ለብይን ቀጠሮ ይዞ እንደነበር ተገልጧል። በዚሁ አግባብ ተካሳሾች እና ከፌዴራል እና ከወልቂጤ አካባቢ የመጡ ጠበቆች በችሎት ተሰይመዋል። የተገኙት ጠበቆችም:_ 1. አቶ ጌዲዎን ቦጋለ፣ 2. አቶ ቶፊቅ በድሩ፣ 3. አቶ ዳውድ ነስሩ፣ 4. አቶ ታሪኩ ዱላ፣ 5. አቶ መውለድ ደግ ስራ ብዙ፣ 6. ወ/ሮ ዘሀራ አክመል፣ 7. አቶ ብዙአየሁ ገ/ዮሀንስ፣ 8. አቶ አብዱልአዚዝ ሁሴን እና 9. አቶ አልሀምዱ ገረመው ናቸው። ግራ ቀኙን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱም የተከሳሽ ጠበቆች የደቡብ ክልል ዐቃቤ ህግ ይህንን ክስ የመመስረት ስልጣን የለውም በሚል ባቀረቡት መቃወሚያ መሰረት የክልሉ ዐቃቤ ህግ ከፌደራል ቃቤ ህግ በተሰጠኝ ውክልና ነው በሚል የተከራከረ በመሆኑ ይህ ውክልና የተሰጠው ለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ እንዲያቀርብ በሚል ትዕዛዝ ሰጧል። ጉዳዩን መርምሮ ብይን ለመስጠትም ቀጠሮ ለሀምሌ 27 ቀን 2015 4:00 ሰዓት ላይ እንዲቀርቡ ሲል ተለዋጭበቀጠሮ ሰጥቷል። አሚማ ለዘገባው ዘቢዳር ቱዩብን በምንጭነት ተጠቅሟል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply