ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ባለበት እስር ቤት የህትመት ውጤት እንዲገባለት ትዕዛዝ ሰጠ

ሰኞ ሐምሌ 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ባለበት እስር ቤት የህትመት ውጤት እንዲገባለት ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ችሎቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለመደበኛ ፍርድ ቤት በታሰረበት እስር ቤት የህትመት ውጤቶች እንዲገባለት እንዲሁም ቴሌቪዥንና ሬዲዮ እንዲፈቀድለት፤ በጠቃው አማካኝነት ባቀረበው አቤቱታ መነሻ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ በሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት ተሰይሟል።

በዚህም መሰረት አቤቱታውን መርምሮ በእስር ቤቱ የቴሌቪዝን አገልግሎት የማይፈቀድ መሆኑን በመግለጽ፤ በህግ የተመዘገበ የህትመት ውጤት ግን እንዲገባላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በሌላ በኩል፤ ጋዜጠኛ ተመስገን በማኔጂግ ዳይሬክተርነት በምሰራበት ፍትህ መጽሔት ድርጅት ሄጄ እንድፈርም ይፈቀድልኝ ሲል ያቀረበውን አቤቱታን በሚመለከት፤ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ተገቢውን ጥበቃ ተደርጎለት በአጃቢ ሄዶ እንዲፈርም ማዘዙን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ዘግባለች።

በዛሬው የችሎት ውሎ ላይ የጋዜጠኛው ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ አለመገኘታቸውም ታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply