ፍቅረ ሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ከ5 መቶ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ነጻ የህክምና ምርመራ አገልግሎት መስጠቱን አስታወቀ፡፡

ፍቅረ ሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል የፋሚሊ ሜዲሲኒ እስፔሻሊስት ዲፓርትመንት ኃላፊ ዶ/ር ትህትና አሸናፊ ለጣቢያችን እንዳሉት ከ5 መቶ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ነጻ የህክምና ምርመራ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

የደም ግፊትና የስኳር ህመም በሀገራችን በከፍተኛት ደረጃ እንዳለ በመግለፅ ቀድሞ ለመከላከል ያመች ዘንድ የምክር አገልግሎት እና ነጻ ምርመራ ለ5 መቶ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡

የፋሚሊ ሜዲሲን ዲፓርትመንት ህክምና በሀገራች ከተቋቋመ 11 ዓመታት እንደሆነዉና በመንግስት ደረጃ በተለያዩ ሆስፒታሎች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ነግረውናል ።

በሃገራችን በግል የጤና ዘርፍ ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ጤናማ ቤተሰብን ለመገንባት የቅድመ መከላከል ላይ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ የቤተሰብ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ብቸኛ ተቋም ነው ተብሏል፡፡

ከብሄራዊ የደምና የቲሹ ባንክ ጋር እንዲሁም ከሆስፒታሉ ሰራተኞች ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት ደም የመለገስ መርሃ ግብር ማካሄዳቸዉንም ዶ/ር ትህትና አንስተዋል፡፡

በልዑል ወልዴ

የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply