“ፍቅሬ ፍቅሬ በዛ እኔ አላማረኝም” – የሀጫሉና የመታሰቢያውና ስጦታው ጋጋታ – አምባቸው ደጀኔ

ይቺ ነገር አላማረችኝም፡፡ ሃጫሉ ሁንዴሳ ከሞተ አራት ወራት ያህል ሆነው፡፡ ቤተሰቦቹ ሀብት በሀብትና ሟቹ ሃጫሉም መታሰቢያ በመታሰቢያ፣ ሐውልት በሐውልት መሆን ከጀመሩ አራት ወራት ሆናቸው፡፡ መታሰቢያ መንገድና ሐውልት ሰውን ከሞት ቢያስነሳ ከሃጫሉ ቀድሞ የሚነሣ ባልነበረ፡፡ መንግሥታችን የሃጫሉን ቤተሰብ እንኮኮ ተሸክሞ መሄድ ነው የቀረው እኮ፡፡

ለኦሮሚያ ሽንጡን ገትሮ ሲታገል የነበረው ሃጫሉ ለኢትዮጵያ እንደታገለ ተቆጥሮ ስጦታውና የመታሰቢያ መንገድና ት/ቤት ስያሜው ከቁጥር በላይ ሆኗል፡፡ መንግሥት በሌላ ነገር እስኪጠረጠር ድረስ ነገርዬው ወሰን አልፏል፡፡ ሰዎቹ ጅሎች በመሆናቸው እንዲህ ዓይነቱ ፍርሀትና ጥርጣሬ ወለድ የስጦታና መታሰቢያ ጋጋታ በሌላ መልኩ ሊያስጠረጥራቸው እንደሚችል አያውቁም፡፡  የሚሠሩትን አጥተው በወንጀላቸው ግርፊያ በተለዬ መልኩ እየጮኹ ነው፡፡ ነገረ ሥራቸው፣ ዐይነ ውኃቸው በሌላ ያስጠረጥራል፡፡

ዘረኝነት እንደሚያሣውር በግልጽ አያየን ነው፡፡ ዘረኝነት ይሉኝታና ሀፍረትን እንደማያውቅ ከወያኔ ባልተናነሰ በኦህዲድና ጭፍሮቹ እየታዘብን ነው፡፡ ዘረኝነት የኅሊናንና የአእምሮን ጤንነት አደጋ ላይ እንደሚጥል እየተመለከትን ነው፡፡ አጃኢብ ነው፡፡

ሰዓረ መኮንን አንድ የጦር ጄኔራል ነበር፡፡ ዶክተር አምባቸው መኮንን የአንድ ክልል ፕሬዝደንት ነበር፡፡ ኢንጂኔር ታከለ ዶማ ማነው ስመኘው በቀለ ትዳሩን ሳይቀር መስዋዕት ያደረገ ታላቅ ባለሙያና የሀገር ባለውለታ ነበር፡፡ እነዚህና ሌሎቹም በተፈጥሮ ሞት እንዳልሞቱና ጠማማው ፖለቲካችን በሸርና ሤራ ጠልፎ እንደጣላቸው ግልጽ ነው፡፡ በሰው ሀብት አባዘራፍ የሆኑት የአዲስ አበባው፣ የፌዴራሉና የኦሮሚያው (ከስምና ቅርጽ በቀር ሁሉም አንድና አንድ ናቸው) መንግሥታት ግን ለአንድ የጎጥ ባለውለታ የሚሠራቸውን አሳጥቶ እሽቅንድር አድርጓቸዋል፡፡ በሰው ሀብት ማዘዝ ቀላል እንደሆነ በነዚህ ይሉኝታቢሶች እየተረዳን ነው፡፡ የሚደረገው ሁሉ ከኪሳቸውና ከጓሯቸው ትርፍ መሬት ቢሆን ምንም አልነበረም፡፡ ነገር ግን ምስኪን ዜጎች በላባቸው ባጠራቀሙት ጥሪታቸው ያስገነቡትን ኮንዶምንየም ሳይቀር ለሀብታሞቹ የሃጫሉ ቤተሰቦች መሸለም የግፎች ሁሉ የበላይ ነው፡፡ እነዚህ ልበ ሥውራን የማይነጋ መስሏቸው ቋታቸውን በግማታቸው ሞልቶ እንዲፈስና በጥምባቱ መቆምም ሆነ መቀመጥ እንዳንችል እያደረጉን ነው፡፡ ‹የህዝን!‹

መካሪ ካላቸውና የሚሰሙ ከሆነ በግፍ ላይ ግፍ መደረቡን አቁመው አሟሟታቸውን እንኳን ለማሳመር አደብ ይግዙ፡፡ ዛሬ የሁላችን የሆነውን የመንግሥትን ሀብትና ገንዘብ እየመዠረጡ ለማንም ማደላቸውን እንደቄንጥ አይተው ሰው ያናደዱንም መስሏቸው እስከዚህ ደረጃ ወርደው የሚሠሩትን ቢያጡም ነገም ሌላ ቀን ነውና የዚህን ጥጋባቸውን የዞረ ድምር ውጤት ያዩታል፡፡

በመሠረቱ ኦሮሞን ኦሮሞ ገድሎት ሲያበቃ ይህን ያህል የሞተን ሰው ዕረፍት ማሳጣት በትንሹ ብልግና ሲበዛ ደግሞ ድንቁርናና የአእምሮ በሽተኛነት ነው፡፡ ጥላሁን አያናና ከበደ ባልቻ የገደሉትን ሃጫሉ፣ ስንሻው ሞላልኝ ምን ይፍጠር ብለው እንደዚህ እንደሚቅነዘነዙም በፍጹም አይገባኝም፡፡ “አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው” እንዲሉ ሆነብኝ፡፡ ግድያው ፖለቲካዊ መሆኑ ጡት ለሚጠባ ሕጻንም በጣም ግልጽ ነው፡፡ የግድያው ሰበበ ድርጊትና የሚፈለገው ውጤት ምንም ይሁን ምን በዚህ ቀሽም ድራማ አማራ እንደሌለበትና ሊኖርበትም እንደማይችል እንኳንስ እግዜር የገዳዮቹ አባት ሰይጣንም ያውቃሉ፡፡ አማራ ኦሮሞን በመግደል የሚያስመዘግበው ድል እንደሌለ ማይሙ አማራ ሳይቀር ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ አማራው መግደል ካለበት ማንንና መቼ መግደል እንዳለበት አሣምሮ ይገነዘባል፡፡ ያ ጊዜ ደግሞ እስካሁን ወደ ታሪክ መድረክ ገና አልመጣም፡፡ ሀገራዊ ሁኔታዎች በዚህ መቀጠላቸው እውነት መሆኑ ካልቀረ ግን ወደፊትና በጣም በቅርቡ የምንፈራው መድረሱ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያም አማራም ሌላውም ንጹሕ ዜጋ በሰላም አብሮና ተባብሮ፣ ተከባብሮና ተፈቃቅዶ መኖር ይኖርበታልና፡፡ ፍርሀትም እንበለው ትግስት ወሰን እንዳለው የምናስታውስበት ዘመን ፊታችን ላይ አለ፡፡ ከሁለት በረቶች የወጡ አጉራ ዘለል በሬዎች እንዲህ ሲፈነጩ ዝም የተባሉት ለበጎ ነው ብለን እንወስዳለን – እንድንማርና ከተመሳሳይ ታሪካዊ ቅብጠት እንቆጠብ ዘንድ፤ ከኃጢኣትና ከክፉ ሥራ እንጠበቅ ዘንድ፤ ለሌላ አይደለም፡፡ እንጂ አንድዬ ሲፈቅድ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ቀሪ ይረዳዋል፡፡ ወገኞቹ ደግሞ “ወሎም የኛ ነው” ሲሉ ሰማሁ ልበል? ጥጋብ የሚወልደው ዕብሪት እኮ ገደብ የለውም፡፡ አዎ፣ አሁን የነሱን ሀፍረት እኛ እያፈርን በግፈኞች ተጨብጠንና ተቆራምደን አለን፡፡

ለማንኛውም አቢይም ሆነ በድኑ ማለትም ቡድኑ ይበርቱ፡፡ ይበርቱናም አማራንና ኢትዮጵያን አሁን ከያዙት በበለጠ ፍጥነትና የክብደት መጠን የጥፋት ተልእኳቸውን ይቀጥሉ፡፡ ትናንት ላይ ሆነን ዛሬን እናውቅ ነበር፡፡ ነገንም እናውቃለን፡፡ በዚህስ አንታማም!

ሃጫሉ ግን ዕድለኛ ነው፤ በአሥር ዓመት ጓደኛው የሤራ ፖለቲካ ድብቅ ሥሌትና የሥሌቱም ታሳቢ ውጤት ምክንያት ተገደለ፡፡ ግን ብዙም የጠቀመው አልመሰለኝም – በተንኮልና በሤራ ማንም ወገን ቢሆን ዘላቂ ጥቅሙን ማስከበር አይቻለውም፡፡ እነ እንቶኔ ኮሮናን ፈልስፈው በዓለም ዙረያ በብርሃን ፍጥነት በመበተናቸው ዕቅዳቸውን እምብዝም እንዳላሳኩት ዓይነት ነው በሀገራችንም የሆነውና እየሆነ ያለው፡፡ (ለሰው ጉድጓድ አትቆፍር፤ ከቆፈርክም ብዙ አታርቀው፤ ለምን ቢባል ቀድሞ የሚገባበትን አታውቀውምና – መባሉን እናስብ)፡፡ ያኔ … ሰኔ 22 ነው 23 2012 ዓ.ም ሃጫሉ መሞቱም ሳይረጋገጥ ገና በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ነቅተው ይጠባበቁ በነበሩ ግሪሣ ቄሮዎች አማራ ከተኛበት እየታደነ ታረደ፡፡ የሚገርም “አጋጣሚ”፡፡ አዲስ አበባ ላይ ከምሽቱ አራት ሰዓት ለተገደለ አንድ የሤራ ፖለቲካ ሰለባ ከምሽቱ አምስትና ስድስት ሰዓት ላይ ከሦስት ቀናት በኋላም ሊሰሙ በማይችሉ ጎረምሶች (ትዕዛዝ ይጠባበቁ የነበሩ ማለትም ይቻላል!) አገር ታመሰች፤ ለብዙ አሠርት ዓመታት የተለፋበት የሀገር ሀብት በእሳት ወደመ፡፡ ያወደሙ ይወድማሉ፤ ቀኑ ቀርቧል!  ምክንያት – ለለአሃዱ በበምግባሩ – ይላልና መጽሐፉ፡፡ በመጪው ጊዜ ቄስ የለ ሸካ፣ ጳጳስ የለ ኢማም፣ ጠ/ሚኒስትር የለ ፕሬዝደንት …. ሁሉም ይበራያል፡፡ ዐውድማው ተለቅልቋል፡፡ የመዳን ቀን ዛሬ ነው፤ በቀጠሮ መዳን ዱሮም አልነበረም፡፡ በጅህ ያለች ጊዜ ናት ወርቅ፡፡ የአሁኑ አጠቃላይ መበስበሳችንና የገባንበት የሙስና አረንቋ ካለደም ማዕበል እንዲህ በቀላሉ ሥርየትን የሚያገኝ አይመስልም፡፡ እግዚአብሔር እንዲመለክ የገንዘብና የሰው ጣዖት መፍረስ አለበት — አምላክ ቀናተኛ ነው!!

[email protected]

Leave a Reply