ስራውን ለማከናወንም ውሉን የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍስሐ ይታገሱ እና የፊልም ዳይሬክተር ሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) የስምምነት ፊርማውን በዛሬው እለት አከናውነዋል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተገለጸው፣ መጽሐፉ ታሪካዊ ይዘት ያለው እንደመሆኑ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ እንዲለውጥ በሚደርግበት ጊዜ የዋናውን መጽሐፍ ታሪክ በማያፋልስ እና በማይበርዝ መልኩ ለመሥራት ከስምምነት ተደርሷል።

ድራማው በአማካይ 45 ደቂቃ ርዝማኔ ሲኖረው ለእያንዳንዱ የድራማ ክፍል (Episode) ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ 863 ሺህ 75 (ስምንት መቶ ስድሳ ሦስት ሺህ ሰባ አምስት) ብር ለመክፈል ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ የድራማውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ማለትም (ከክፍል1-12) የተጠናቀቁ ሥራዎችን እንዲሁም በቀጣይ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ (48 ክፍሎች) አጠናቅቆ ለማስረከብ “ሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን” ከኢቢሲ ጋር በዛሬው ውል እለት ተፈራርመዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም
Source: Link to the Post