You are currently viewing “ፍቅር እስከ መቃብር” በተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ሊተላለፍ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ የኢቢሲ ዋና ሥራ…

“ፍቅር እስከ መቃብር” በተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ሊተላለፍ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢቢሲ ዋና ሥራ…

“ፍቅር እስከ መቃብር” በተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ሊተላለፍ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍስሐ ይታገሱ እና የፊልም ዳይሬክተር ሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) የስምምነት ፊርማውን በዛሬው እለት አከናውነዋል። በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተገለጸው፣ መጽሐፉ ታሪካዊ ይዘት ያለው መፅሀፍ እንደመሆኑ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ እንዲለወጥ በሚደርግበት ጊዜ የዋናውን መጽሐፍ ታሪክ በማያፋልስ እና በማይበርዝ መልኩ ለመሥራት ከስምምነት ስለመደረሱ ተገልጧል። በአማካይ የ45 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ድራማ እያንዳንዱን የድራማ ክፍል ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ 863 ሺህ 75 (ስምንት መቶ ስድሳ ሦስት ሺህ ሰባ አምስት) ብር ለመክፈል ስምምነት ላይ መደረሱ ተመላክቷል። በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ የድራማውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ማለትም (ከክፍል1-12) የተጠናቀቁ ሥራዎችን አጠናቆ ለማስረከብ ውል ተወስዷል። በቀጣይ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ደግሞ 48 ክፍሎችን ሙሉ በሙሉ አጠናቅቆ ለማስረከብ ሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን ከኢቢሲ ጋር የካቲት 14/2015 ውል ስለመፈራረሙ ከኢቢሲ ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply