“ፍቅር እስከ መቃብር” በተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ሊመጣ ነው!ስራውን ለማከናወንም ውሉን የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍስሐ ይታገሱ እና የፊልም ዳይሬክተር ሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) የስ…

“ፍቅር እስከ መቃብር” በተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ሊመጣ ነው!

ስራውን ለማከናወንም ውሉን የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍስሐ ይታገሱ እና የፊልም ዳይሬክተር ሰውመሆን ይስማው (ሶሚክ) የስምምነት ፊርማውን በዛሬው እለት አከናውነዋል።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተገለጸው፣ መጽሐፉ ታሪካዊ ይዘት ያለው እንደመሆኑ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ እንዲለውጥ በሚደርግበት ጊዜ የዋናውን መጽሐፍ ታሪክ በማያፋልስ እና በማይበርዝ መልኩ ለመሥራት ከስምምነት ተደርሷል።

ድራማው በአማካይ 45 ደቂቃ ርዝማኔ ሲኖረው ለእያንዳንዱ የድራማ ክፍል (Episode) ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ 863 ሺህ 75 (ስምንት መቶ ስድሳ ሦስት ሺህ ሰባ አምስት) ብር ለመክፈል ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ የድራማውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ማለትም (ከክፍል1-12) የተጠናቀቁ ሥራዎችን እንዲሁም በቀጣይ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ (48 ክፍሎች) አጠናቅቆ ለማስረከብ “ሰው መሆን ፊልም ፕሮዳክሽን” ከኢቢሲ ጋር በዛሬው ውል እለት ተፈራርመዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረሃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply