ፍትህን እያሻሻጠ ያለው ክልል! አሸናፊ ገናን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሀምሌ 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ክልል ተቋማዊ ውቅሩ ሞግዚታዊ…

ፍትህን እያሻሻጠ ያለው ክልል! አሸናፊ ገናን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሀምሌ 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ክልል ተቋማዊ ውቅሩ ሞግዚታዊ አስተዳደር መሆኑን በትክክል አረጋግጧል። አርቲፊሻል ማኔጅመንቱ ህግን አስከብራለሁ፤ አከብራለሁ ቢልም ዕውነታው ግን በአብይ አህመድ መንግስት የመጀመሪያው የስጋት ቀጠና የነበረው አማራው ላይ ነበር። ስለሆነም የክልሉን ስልጣን በዋናነት እየዘወረው ያለው ሃይል በአማራ ስም የተሰየመው ፕሬዘዳንት ይልቃል ከፈለ ሳይሆን የአራት ኪሎው ሰውየ ነው። በህግ ተርጓሚው እና በአስፈፃሚው አካል መካከል ትልቅ የሆነ የፓለቲካ ልዩነት ቢኖርም የክልሉ ስልጣን ግን መጫወቻ ሆኗል። ፍ/ቤት ነፃ ያላቸውን የአሻራ እና የንስር ሚድያ ጋዜጠኞችን ከመንገድ ላይ አፍኖ ወደ ፌደራል መላካቸውን ስንሰማ ክልሉ ውስጥ ያለውን ያልተገደበ ጣልቃ ገብነት ያሳያል። ህግን እና ስርዓትን መድፈቅስ እንዴት መንግስት ያስብላል?? ስለሆነም መንግስት ሆይ ከተራ ብሺሺቅና ውንብድና ብትወጣ ትርፉ ለእናንተው ነው። ጋዜጠኞችንና ጋዜጠኛን ማሰር ለስርዓቱም አይበጅ!! በተለይም በፍትህ የተለቀቁ ተጠርጣሪዎችን በህግ ሺፋን ስም ማሰር የስርዓቱን በህዝብ መታመን አደጋ ላይ ጥሎታል። በሺወች የታፈኑ የአማራ ልጆች አሁንም እስር ላይ ናቸው፤ አንዳንዶችም የደረሱበት አይታወቅም። የአማራን ህዝብ ተራ ለብሺሺቅ ፓለቲካ እና ለጥሬ ስልጣን ማስቀጠያ በማድረግ የሚቀጥል ስልጣን የለም። ክልሉ ላይ ያለውን ስር የሰደደ የተገዥነት ስሜት በጊዜ መፍትሔ ብትሰጡት መልካም ነው። ካልሆነ የእናንተም ስልጣን አይኖርም። የአማራ ህዝብ ላይ የተጫኑ የጭቆና ቀንበሮች በሙሉ የቁርጠኝነት ትግልን ብቻ የሚፈልጉ ናቸው። ስለዚህ ህዝባችን በትንኝ ንክሻ ከመጮህ ይልቅ ለመዋጥና ለመሰልቀጥ ከተዘጋጀው ዘንዶ ራሱን ይጠብቅ። የታፈኑ አማራወችን ሁሉ ፍቷቸው!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply