You are currently viewing ፍትህአለው አሰፋ የተባለ የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእህት ልጅ ታፍኖ ደብዛው ከጠፋ ቀናት መቆጠሩ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      ጥር 19 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበ…

ፍትህአለው አሰፋ የተባለ የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእህት ልጅ ታፍኖ ደብዛው ከጠፋ ቀናት መቆጠሩ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበ…

ፍትህአለው አሰፋ የተባለ የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእህት ልጅ ታፍኖ ደብዛው ከጠፋ ቀናት መቆጠሩ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ፍትህአለው አሰፋ የተባለ የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእህት ልጅ ከጥር 15/2015 ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ ጀምሮ ታፍኖ ደብዛው ከጠፋ ቀናት መቆጠሩ ከቤተሰብ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ነዋሪነቱ በባህር ዳር ከተማ የሆነው ወጣት ፍትህአለው አሰፋ ጉባላ በተባለ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ገብቶ እየሰለጠነ እንደነበር ተገልጧል። የጽሁፍ ፈተና ተፈትኖ ወደ ፊልድ ለተግባር ስልጠና በሄደበት ነው የታፈነው። ፍትህአለው አሰፋ ወደ አየር መንገድ መሄጃ ዘጌ መገንጠያ አካባቢ ከሌሎች ሰልጣኞች ጋር በመሆን የተግባር ልምምድ እያደረገ ሳለ:_ 1) በፓትሮል የመጡ ከ4 በላይ በሚሆኑ የልዩ ኃይል ዩኒፎርም በለበሱ አካላት እንዲሁም 2) በጥቁር ኮብራ የተሳፈሩ ሌሎች ሲቪል በለበሱ ደህንነቶች አፈና የተፈጸመበት መሆኑ ተገልጧል። ከዐይን እማኞች የተገኘው መረጃ እንዳመለከተውም ወጣት ፍትህአለውን በፓትሮል ላይ ጭነው ሲወስዱ አሰልጣኙ “የት እና ለምን ትወስዱታላችሁ? ፣ እኔንኮ ተቋሙ እና ቤተሰብ ሰልጣኝ ተማሪውን የት ጣልከው ብለው ይጠይቁኛል” ሲላቸው “አንተንም እንጭንሃለን” በማለት ሲያስፈራሩት ዝምታን መምረጡን ተናግረዋል። ጥር 15/2015 ከ5 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በቤተሰብ በኩል ሲደወል ስልኩ ክፍት ነበር፤ ነገር ግን እየጠራ የሚያነሳው አልነበረም። በእለቱ ከቀኑ 8 ሰዓት በኋላ ስልኩ ስለመዘጋቱ ተመላክቷል። ጥር 16/2015 የመንግስት አካላት አፍነው የወሰዱት ስለመሆኑ ለአሽከርካሪዎች አሰልጣኝ በመደወል ለማረጋገጥ ተችሏል። አፍነው የወሰዱትም ከስልካቸው ፎቶውን በማውጣት ካመሳከሩ በኋላ ወጣ ካለው የተግባር ማሰልጠኛ ወደ ባህር ዳር ከተማ ይዘውት መግባታቸው ተገልጧል። በወቅቱም ሲቪሎች ካስያዙ በኋላ ወደ ባህር ዳር ኤር ፖርት ሲሄዱ፣ ባለ ፓትሮል ልዩ ኃይሎች ግን ጭነት ወደ ከተማ ገብተዋል ይላሉ የአሚማ የመረጃ ምንጮች። ይሁን እንጅ እስካሁን ድረስ ፍትህአለው የት እንደታሰረ የታወቀ ነገር የለም፤ ፍ/ቤትም አልቀረበም፤ አሸናፊ አካሉም ከታፈነ ድፍን 12ኛ ቀኑን ይዟል። ይህ አካሄድ አሳሳቢ እና ፍጹም ከህጋዊ መስመሩ የወጣን መንግስታዊ አፈና እና እገታን እንድንለማመድ እያደረጉን እንገኛለን ሲሉ ነዋሪዎች የታፋኝ ቤተሰቦች እየገለጹ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply