
ፍትህ ለታዳጊው ወጣት ሃብተማርያም ሞላ! ግንቦት 07 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ቀበሌ 07 ተወልዶ ያደገው ባለ ሙሉ ሰብዕና ባለቤቱ ሀብተማርያም ሞላ ፖሊስ በግል ቂም ተነሳስቶ የጦስ ዶሮ ማድረጉን አሻራ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፊት በአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ስራ አስፈፃሚ ሁኖ ለአመታት ሲሰራ መቆየቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።በአገዛዙ ከታፈነ ከአንድ ወር በላይ አስቆጥሯል።ከአፈናው መልስ በባህርዳር ሰባታሚት ወሀኒ ቤት ያለ ምንም ፍርድ ወራቶች እያስቆጠረ ነው። በባህርዳር ከተማ ብዙ ሰዎች ለሃብተማርያም ሞላ ፍትህ እንዲያገኝ ጥያቄ ቢያቀርቡም ሰሚ አጥተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለውጥ እንዲመጣ የሚጠይቁ የባህርዳር ከተማ ተወላጅ ወጣቶች በስርዓቱ እየተገፉ ከተማዋን ለቀው እየወጡ መሆኑን እየተነገረ ነው። ፍትህ ለታዳጊው ወጣት ለታጋይ ሀብተማርያም ሞላ!!! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post