You are currently viewing ፍትህ ያጣው የፓስተር ቢንያም እስር ጉዳይ! የካቲት 24ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባለፈው አርብ የካቲት 17 ቀን ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት 33 ጠበቆች…

ፍትህ ያጣው የፓስተር ቢንያም እስር ጉዳይ! የካቲት 24ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባለፈው አርብ የካቲት 17 ቀን ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት 33 ጠበቆች…

ፍትህ ያጣው የፓስተር ቢንያም እስር ጉዳይ! የካቲት 24ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባለፈው አርብ የካቲት 17 ቀን ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት 33 ጠበቆች ቀርበን ለፓተር ቢንያም የ5 ሺህ ብር ዋስትና አስይዞ እንዲወጣ ተፈቀደ። ፖሊስ ከሰዓት በኋላ በዛው አራዳ ምድብ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ጠይቄአለሁ በማለት አለቅም አለን። የይግባኝ ክርክር የዛኑ እለት አቀረብን። ለሰኞ የካቲት 20 ብይን ለመስጠት ተቀጠረ። በ20 ጉዳዩን ያየው ከፍተኛ ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በማፅናት እንዲወጣ አዘዘ። አሁንም ፖሊስ ሰበር ችሎት ጉዳዩን አቀርባለሁ እና ፓስተሩን አለቅም አለ። ሰበር ችሎት ጉዳዩ ምንም የህግ ስህተት የለበትም ይውጣ አለ። አሁን የይግባኝ አማራጮች አለቁ። እኛም መጀመሪያ ዋስትና የፈቀደው ፍ/ቤት በመሄድ የፍ/ቤቱ ትእዛዝ አለመከበሩን ፓስተር ቢንያም እስካሁን በእስር ላይ መሆኑን በመጥቀስ አቤቱታ አቀረብን። ቀርበህ አስረዳ የተባለው ፖሊስ ቀርቦ “እኛ ለቀነዋል” ብሎ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ለፍ/ቤቱ አቀረበ። ይህ ሀሰት ነው ሌላ ቦታ ወስደውት ነው ብለን ለፍ/ቤት አስታውቀን ።ፖሊስ ፓስተሩን ይዞ ን/ስ/ላፍቶ ክከተማ ፖሊስ መምሪያ ወስዶት ነበር። ዛሬ ደግሞ በክ/ከተማው ከተማ ነክ ፍ/ቤት አቀረበው። ፍ/ቤቱ በ2 ሺህ ብር ዋስትና ይውጣ አለ። ፖሊስ እንደተለመደው ይግባኝ እጠይቃለሁ አለቅም አለ። የይግባኝ ሰሚው ችሎት የስር ፍ/ቤቱን ውሳኔ አፀናው። ሰበር በዚህ ሰዓት ሰበር እንውሰደው ብለው ወስደውት ይግባኙን እየጠበቅን ነው። ፍ/ቤቱ ምንም አለ ምን ግን አንድ ነገር እርግጠኛ መሆን ይቻላል። ፖሊስ ሊለቀው እንደማይፈልግ እና እንደማይለቀው። አዲስ አበባ ውስጥ 11 ክ/ከተማዎች አሉ። በእያንዳንዱ ክ/ከተማዎች ባሉ ፍ/ቤቶች እያቀረቡ ቢያንገላቱት የዋስትና ገንዘብ ብቻ በማስያዝ ገንዘቡን ይጨርሱታል፣ እሱን እና ሌላውን ህብረተሰብ ደግሞ በፍትህ ስርዓቱ የማያምን ፈሪ ያደርጉታል። በፖሊስ የየፈፀሙ ከባድ ህግ ጥሰቶች:- 1. በወ/መቅጫ ሥነ ሥርዓቱ መሰረት የዋስትና መብት የተነፈገ ሰው ይግባኝ ይላል እንጂ ፖሊስ ዋስትናን ለማስከልከል ይግባኝ የሚጠይቅበት ህግ የለም። 2. ፖሊስ ይግባኝ ቢጠይቅ እንኳን ያንን የሚሽር የበላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ወይም ጊዜአዊ እግድ ሳያቀርብ ይሄን ያህል ቀን ዋስትና የተፈቀደለትን ሰው በማንአለብኝነት ማሰር አይችልም። 3. በተመሳሳይ ጉዳይ የተጠረጠረን ሰው ከቦታ ቦታ እየቀያየሩ በማሰር የተለያዩ ፍ/ቤቶች ማቅረብ የዜጎችን ሕገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ እና ህጋዊ ያልሆነ አካሄድ ነው። 4. ሰበር የሚቀርቡ መዝገቦች መሰረታዊ የሕግ ስህተትን ለማሳረም እንጂ ለእንደዚህ አይነት የዋስትና ጥያቄ አይደለም። ~ ብሩክ ደረጀ (ጠበቃ እና ሕግ አማካሪ) “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply