ፍትሕ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ!_ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን የማፈን ዓለማቀፍ የሕግ ጥሰት ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ…

ፍትሕ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ!_ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን የማፈን ዓለማቀፍ የሕግ ጥሰት ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 23/2014 እስከ ማክሰኞ ሐምሌ 26/2014 የሚቆይ ዘመቻ ፍትህ ለጋዜጠኛ ደሳለኝ ሁለተኛ ዙር ቀጥሏል። የዘመቻ ፍትህ አስተባባሪዎች የሚከተለውን መረጃ አጋርተዋል:_ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላለፉት ሁለት ወራ ከአምስት ቀናት ሀሳቡን በነፃነት በመግለፁ ብቻ በፃፋቸው ፅሁፎች ምክንያት በእስር ላይ እንዳለ ይታወቃል። የክስ ይዘቱ እየተቀያየረ ረብ በሌለው ምክንያት ሁለት ወራትን በእስር ቆይቷል። ሐሙስ ሐምሌ 21/2014 በ 100 ሽህ ብር በዋስትና እንዲወጣ በነበረው ቀጠሮ የፌዴራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዋስ መውጥት የለበትም በእስር ቤት ሆኖ ክሡን እንዲከላከል መወሠኑ ይታወቃል:: በመሆኑም ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ የሥራ ባልደረቦቹ፣ የሞያ አጋሮቹና የሞጋቹ ጋዜጠኛ ጉዳይ ያገባናል ያሉ ወገኖች በጋራ ዘመቻ_ፍትሕ በሚል መሪ ቃል ድምፃችን ማሠማት ጀምረናል። ከዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 23/2014 ዓ.ም. ጀምሮ ጋዜጠኛ ተመስገን ፍ/ቤት እስከ ሚቀርብበት ሐምሌ 26/2014 ማክሰኞ ጠዋት ድረስ ዘመቻ_ፍትሕ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የሚቆይ ይሆናል። ሀሳብን በነጻነት ስለመግለጽ እቆረቆራለሁ ያሉ በርካቶች የዘመቻው ተባባሪ መሆናቸውን ከዚህ ቀድሞ እንዳየነው አሁንም ከዘመቻው ጎን እንደሚሆኑ ለመሆን ከወዲሁ ፈቃደኝነታቸውን አሳይተዋል። እርስዎም አጋርነትዎን እንዲያሳዩ ጥሪው ቀርቦልዎታል። ዓላማው ከየትኛውም የፖለቲካ አመለካከት ጋር ስለማይገናኝ ሀሳብን በነጻነት በመግለፅ መብት የሚያምን ሁሉ የዘመቻው ተሳታፊ እንዲሆን በአክብሮት እንጠይቃለን። የጋዜጠኛ ተመስገንን ምስል ፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግ፣ እርሱንና እየደረሰበት ያለውን ግፍ የሚመለከት አጫጭር መልዕክት በማስተላለፍ፣ በመናገር መብት ላይ ያለንን አቋም በመጋራት፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተገኝተን ጋዜጠኛውን በመጎብኘት፣ እየሆነ ያለውን ለሚመለከታቸው አካላት በማድረስ እንዲሁም ይበጃል የምንለውን የግል ሀሳብ በማዋጣት የዘመቻው አካል እንሁን። የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጉዳይ የአንድ ግለሰብ አጀንዳ አይደለም። ጉዳዩ በነፃ ጋዜጠኝነት ሙያ ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው። ጉዳዩ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን የማፈን ዓለማቀፍ የሕግ ጥሰት ነው። ጉዳዩ የግፉዓን ልሳን የሆነን አንደበት በመዝጋት የሚሊዮኖችን መብት የመርገጥ ሙከራ ነው። ሁላችንም ለሀሳብ ነፃነት ዘብ ልንቆም ይገባል!! ግልባጭ፦ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ለመገናኛ ብዙሐን ባለሞያ ማህበራት ለጋዜጠኞችና ለማኅበረሰብ አንቂዎች ለሲፒጄ ለአሜሪካ ኤምባሲ አዲስ አበባ ለአውሮፓ ሕብረት ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል በአዲስ አበባ ላሉ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት

Source: Link to the Post

Leave a Reply