ፎሬክስ ትሬዲንግ እና በስሙ የሚሰራው ማታለል

ፎሬክስ ትሬዲንግ የኦንላይን ስራ እንደሆነ ሲነገር ብር ኢንቨስት አድርጉና ትረፋማ ሁኑ  የሚሉ ማስታወቂያዎች በስፋት ሲሰሙ ይስተዋላል፡፡

በሶሻል ሚዲያ  ስያሜአቸው  ከፎሬክስ ትሬዲንግ ጋር የተያያዘ ቢሆንም  “ትሬድ በማድረግ አትራፊ ትሆናለች” የሚል ቃል በመግባት ከሰዎች ገንዘብ እያስላኩ የማጭበርበር ስራ የሚሰሩ እንዳሉም ይናገራሉ።

በአንድ ወር ውስጥ ስልጠናውን በመውሰድ በቂ እውቀት እና ትርፋማ እንደሚያደርጋቸው የሚነሳው ስራ ምን ያህል ልክ ይሆን?

ጣቢያችን ለመሆኑ ፎሬክስ ትሬድ ምንድነው እንዲሁም የሚደረጉት ማጭበርበሮች ምን ይሆኑ  በሚለው ላይ ማጣሪያ አድርጓል

ፎሬክስ አለም ያለ የንግድ ስርዓት ሲሆን በተለይም የውጭ ሃገር ዜጎች ኢንቨስት በማድረግ  በስፋት ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡

በውጭው አለም ፎሬክስ ላይ በዘርፉ ብዙ አመት እውቀት ያላቸው 60 እና ከዛ በላይ አመት ትንበያ የሚያደርጉ ሰዎች ኢንቨስት እንደሚያደርጎ ተነስቷል።

ታዲያ ሀገራችን ላይ በአንድ ወር ስልጠና ኢንቨስት አድርጋችሁ ብር ሰብስቡ የሚሉ የተጋነኑ ማስታወቂያዎች የማጭበርበሪያ እና የማታለያ ዘዴ ናቸው ይላሉ አብዛኛው የዘርፉ ባለሞያዎች።

በተለይም 10 ሺህ ብር ኢንቨስት በማድረግ  170 ወይም 180  ሺህ ብር አግኙ የሚሉ ማስታወቂያዎች የማታለያ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ፎሬክስ ውስበስብ የሆነ ነገር እንደሆነ ሲነሳ  በትንሽ ስልጠና በመልመድ ትርፋማ መሆን እንደማይቻል ተነስቷል

ማህበረሰቡም በዚህ ሳቢያ ብዙ ማጭበርበሮች እንደደረሱበት ጣቢያችን ያደረገው ምልከታ ያመለክታል፡፡

በተለይም በስፋት የውጭ ሀገር ሰዎች በጉዳዩ ላይ እየተንቀሳቀሱ ብር እንደሚያስልኳቸው ገልፀው ገንዘቡን ለመላኪያ የሀገር ውስጥ ባንክ እንደሚጠቀሙ ይናገራሉ።

ከዛ ባለፈም ሶሻል ሚዲያ ስፖንሰር ያደረጋቸው  ሰዎችን ማስታወቂያ እንዲሰሩ በማድረግ ነገሩ የተለየ እንዲመስል የማድረጉ ሁኔታዎችም እንዳሉም ተገልጧል፡፡

ከዛ በኋላ ገንዘባቸው እንደሚለስላቸው ሲጠይቁ ግን አንዴ ኢንቨስት የተደረገ በመሆኑ መመለስ እንደማይቻል እንደሚነገራቸውም ይናገራሉ።

እንዲሁም የተለያዩ የኮይን ስያሜ በመያዝ ብዙ ማጭበርበሮች በሶሻል ሚዲያው እንደሚስሩ የተነሳ ሲሆን ነገር ግን ሁሉም አነድ እንዳለሆነም ተነግሯል

በዚህም ማህብረሰቡ ካላስፈላጊ መጭበርበሮች እራሱን እንዲጠብቅ እና ፎሬክስን የመጠቀም ፍላጎት ያለውም ካለምንም ክፍያ መጀመሪያ በዲሞ አካውንት መለማመድ እንደሚገባውም ተመላክቷል፡፡

ጣቢያችን ለመረጃው የምጣኔ ሃብት እንዲሁም በዘርፉ  ባለሞያ የሆነውን አቶ መቆያ ከበደ እንዲሁም በኢትዮጵያ የቢትኮይን እና መሰል ነገሮች ላይ አስተማሪ የሆነውን አቶ ቃል ካሳን እንደ ግብዓት ተጠቅሟል፡፡

ለአለም አሰፋ

ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply