ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ እና ግሪን ኬር ናቹራልስ በጋራ የቡና ዘይት ለማምረት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ እና ግሪን ኬር ናቹራልስ ኃ.የተ.የግ.ማ በጋራ ለመስራት…

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ እና ግሪን ኬር ናቹራልስ በጋራ የቡና ዘይት ለማምረት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ እና ግሪን ኬር ናቹራልስ ኃ.የተ.የግ.ማ በጋራ ለመስራት በዛሬው ዕለት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ግሪን ኬር ናቹራልስ በ2018 የተመሠረተ በተፈጥሮ ዕፅዋት ህክምና የሚሰጥ ክሊኒክ ነው። በተለይ ደግሞ ከቡና ዘይትን በማምረት ለህክምና ያውላል።

በዛሬው ዕለትም ከፐርፐዝ ብላክ ጋር በቡና ዘይት ኢንዱስትሪ ውስጥ በጋራ ኢንቨስት ለማድረግ ተስማምተዋል።

በተጨማሪም የቡና ዘይት የችርቻሮ ስርጭትን በጋራ ለመስራት እና የቡና ተረፈ ምርቶችን እንደገና በማቀነባበር ረገድ ባሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ነው የተገለፀው።

በዚህ ስምምነት ተጠቃሚው ገበሬው ነው የተባለ ሲሆን፤ከሚገኘው ትርፍ 90 በመቶውን ገበሬው ቀሪውን 10 በመቶ ደግሞ ሁሉቱ ድርጅቶች የሚካፈሉት መሆኑን የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍስሀ እሸቱ ገልጸዋል።

የግሪን ኬር ናቹራልስ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ግዛው በቀለ ከ 1መቶ ኪሎ ቡና 5 ሊትር የቡና ዘይት እንደሚገኝ ገልፀው፥ በአለም አቀፍ ገበያ አንድ ሊትር በ1ሺህ ዶላር የሚሸጥ መሆኑን በማንሳት በዘርፉ መስራት ለአገር ኢኮኖሚ የሚጠቅም መሆኑን ነው የገለፁት።

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ እና ግሪን ኬር ናቹራልስ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ዙሪያ ያሉ ጉዳዮች ወደፊት በስፋት የሚገለፁ መሆናቸውን ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።

በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply