ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ “የጋራ ቤት ገንቢዎች አገልግሎት” የተሰኘ የሪል እስቴት ቢዝነስ ይፋ አደረገ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይሰራሉ የተባሉ ቤቶች በወቅቱና በተባለው የገንዘብ መጠን አልጠናቀቅ እያሉ በሪልስቴት አልሚዎችና በገዥዎች መካከል አለመግባባቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡

ከዚህም አልፎ በሁለቱ አካላት መካከል አለመተማመን እንዲሰፍን ስለማድረጉም ይነሳል፡፡

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ይህንን ችግር የሚቀንስ እና የነበረውን አሰራር ሊቀይር የሚችል አዲስ ሞዴል ይዞ መምጣቱን ይፋ አድርጓል፡፡

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጰያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ እንደሚሉት፣የጋራ ቤት ገንቢዎች አገልግሎት ከዚህ ቀደም ሲሰራበት ከነበረው የቤት ልማት ለየት ባለ መልኩ ቤት ፈላጊዎች የቤታቸውን አጠቃላይ ገፅታና አሰራር ፣ጥራት ፣ መገኛ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠት የሚያስችላቸው ከመሆኑም ባሻገር የፋይናንስ ሂደቱንም በቀጥታ የሚቆጣጠሩት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህም በቤት አልሚዎች ይያዝባቸው የነበረውን የተጋነነ የትርፍ ማርጅን ከማስቀረቱም በተጨማሪ መተማመንን ለመገንባት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

ዳውንታውን፣ ሚድታውን ፣ሰብረብ ፣ ዲያስፖራ፣ ሲንግል ፋሚሊ እንዲሁም የንግድ ቤቶች የማደራጃ ዘርፎች እንደሆኑ ታውቋል፡፡

ፐርፐዝ ብላክ በቀጥታ የፋይናንስ ጉዳዮች ላይ እንደማይገባ የተናገሩት ዶ/ር ፍስሃ ከዛ ይልቅ ህጋዊ ሁነቶችን ማስፈጸም ፣ዲዛይንና የዋጋ ዝርዝር ማቅረብ ፣የግንባታ ስራ አስተዳደርና ንብረት አስተዳደር ላይ እንደሚሰራና እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

ለዚህ አገልግሎት የሚሆኑ መሬቶች በበቂ ሁኔታ መኖራቸውን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚው በተለይም ወሰን አካባቢ መሬት ተገዝቶ የመሰረት ድንጋይ እንደተጣለ እና በሌሎችም አካባቢዎች መሬት ለመግዛት በዚደት ላይ እንዳለም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በመሬት ጉዳይ ብዙም ችግር እንደሌለ የተናገሩት ዶ/ር ፍስሃ ከ200 በላይ የመሬት ባንክ ዳታቤዝ መኖሩንና አሁንም በቂ መሬት እንዳለ ከሚመጣልን የግዙን ጥያቄ መገንዘብ ችለናል ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply