ፐርፐዝ ብላክ የባንክ ሒሳቤ የታገደው በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሚለውን የሕግ ደንጋጌ መሠረት ተደርጎብኝ ነው አለ።ይህ ሆን ተብሎ የተፈጠረ የድርጅቱን ስም…

ፐርፐዝ ብላክ የባንክ ሒሳቤ የታገደው በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሚለውን የሕግ ደንጋጌ መሠረት ተደርጎብኝ ነው አለ።

ይህ ሆን ተብሎ የተፈጠረ የድርጅቱን ስም ለማጥፋት በማሰብ የተደረገ የስም ማጥፋት ድርጊት ነውም ብሏል።
በተቋሙ የቀረበው ክስ በምንም አይነት መንገድ ተቀባይነት የለውም ብሏል ፐርፐዝ ብላክ።

በግብርና፣ በሪል እስቴትና በሌሎችም የተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚገኘው ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ
የባንክ ሒሳቦች የታገዱበት፣ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሚለውን የሕግ ደንጋጌ መሠረት አድርጎ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶ/ር ፍሰሐ እሸቱ እንደጠቆሙት፣ ለድርጅቱ ግልባጭ ባይደረግለትም፣ ለባንኮች ከተጻፈው ደብዳቤ ለመረዳት እንደቻሉት፣ በሕገወጥ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ በሚል መሆኑን ለማየት መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሐ እሸቱ የኩባንያቸውና የግል የባንክ ሒሳባቸው ያለ ምንም የክስ ደብዳቤና ማስጠንቀቂያ እንደተዘጋባቸውና ይኸም ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አካውንታችን ከተዘጋ በኋላም የተለያዩ ክሶች እየቀረቡብን ይገኛል ብለዋል።

ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ አካውንቴ መዘጋቱ እንዳለ ሆኖ ለመዘጋቱ ምክንያት ተብሎ ከመንግስት አካል የቀረበልኝ አሳማኝና ተቀባይነት የለውም ብሏል።

የፐርፐዝ ብላክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሀ እሸቱ ለሀገሬ እየሰራሁ ባለበት ሁኔታ እንደዚህ አይነት ግፍ ይደርስብኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም ሲል በተሰጠ መግለጫ የድርጅቱንና የግል የባንክ አካውንታቸው ጭምር በመዘጋቱ ለሰራተኛ ደሞዝና የስራ ማስኬጃ ወጭዎችን መክፈል ችግር ውስጥ መግባታቸውን ዋና ስራ አስፈጻሚው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply