ፑቲን ለኪም ጆንግ ኡን መኪና በስጦታ መልክ አበረከቱ፡፡የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ዘመናዊ መኪና በስጦታ ማበርከታቸው ተሰምቷል፡፡ሩሲያ ሰራሽ ናቸ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/eo_Nv654JdCuHuw20nhzHOWdU3lemyq0RJDLMDpiIWjraeUdx8T-lfFu_AtbsRp5vtepZyDyHqNhyYkr2z3YITNemjSc7SO68ZaaNZ0-e-xHs6zpCwrpg63KmL1_ftMCUwgk21pL9FjuyZarGNOyXIOu_vjFa0CMrbI_on9ce3TrqIyZOMjXAL_ZuxWKe81byEGH0F8niqPOc93Q9-J3kVPT6w-iSA05LM_4rIFS8EBr9zsIzVWz8t6bHxHQPyync59tKzkrUNvGEPFDrwL2sLbnbNwdZHcO0G9QK366qUDUbVmWoWPcTIq6RLWUF__m6kB93fcnY24xsyTKZDBhHw.jpg

ፑቲን ለኪም ጆንግ ኡን መኪና በስጦታ መልክ አበረከቱ፡፡

የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ዘመናዊ መኪና በስጦታ ማበርከታቸው ተሰምቷል፡፡

ሩሲያ ሰራሽ ናቸው የተባሉት ተሽከርካሪዎች ምን አይነት ሞዴል እንዳላቸው ባይገለጽም ኪምና እህታቸው ለግል እንቅስቃሴያቸው እንዲጠቀሙባቸው የተበረከቱ መሆናቸውን የሰሜን ኮሪያው ኬሲኤንኤ ዘግቧል።

የፑቲን ስጦታ የመንግስታቱ ድርጅት ለፒዮንግያንግ ምንም አይነት የትራንስፖርት ተሽከርካሪ እንዳይቀርብ ያሳለፈውንና ሀገራቸውም የደገፈችውን ውሳኔ የጣሰ ነው ብሏል አሶሼትድ ፕረስ በዘገባው።

በመስከረም ወር 2023 በሩሲያ ጉብኝት ሲያደርጉም ፕሬዝዳንት ፑቲን ከ2018 ጀምሮ የሚጓዙባትን “ኡሩስ” ሊሞዚን እንደወደዷት መግለጻቸውና ፑቲንም ከኋላ ወንበር እንዲቀመጡ ጋብዘዋቸው አብረው ሲጓዙ መታየታቸው ይታወሳል።

ምዕራባውያን ፊታቸውን ያዞሩባቸው ፑቲን እና ኪም በተለይ ሩሲያ በ2022 በዩክሬን ጦርነት ከከፈተች በኋላ ወዳጅነታቸውን ማጠናከራቸው ተገልጿል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply