ፑቲን በኮንሰርት አዳራሽ የተፈፀመው የሽብር ጥቃት በጥንቃቄ የተደራጀ ብቻ ሳይሆን ‘አላማ ያለው እልቂት ነው’ ብለውታልፕሬዝዳንት ፑቲን መጋቢት 24 ብሄራዊ የሀዘን ቀን ሲሉ አውጀዋል።አዳዲስ…

ፑቲን በኮንሰርት አዳራሽ የተፈፀመው የሽብር ጥቃት በጥንቃቄ የተደራጀ ብቻ ሳይሆን ‘አላማ ያለው እልቂት ነው’ ብለውታል

ፕሬዝዳንት ፑቲን መጋቢት 24 ብሄራዊ የሀዘን ቀን ሲሉ አውጀዋል።

አዳዲስ ጥቃቶችን በመፍራት በሁሉም የሩስያ ክልሎች የጸጥታ እርምጃዎች መጨመሩን ፑቲን ተናግረዋል።

በሞስኮ ክልል በሚገኘው ኮንሰርት አዳራሽ የሽብር ጥቃት የፈጸሙ በቀጥታ የተሳተፉ ወንጀለኞች ወደ ዩክሬን ሲጓዙ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ተናግረዋል።

ፑቲን በክሮከስ ከተማ የኮንሰርት አዳራሽ የሽብር ጥቃት አስተባባሪዎች ‘እንደ ናዚዎች አንድ ወቅት’ን ‘የሚያሳይ ግድያ እና ደም አፋሳሽ የማስፈራራት ስራ አዘጋጅተዋል’ ብለዋል።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን የሽብር ጥቃት አላማ በህብረተሰቡ ውስጥ አለመግባባትን መፍጠር ነበር ብለዋል።

የሩሲያ ልዩ አገልግሎት የሞስኮ ኮንሰርት አዳራሽ አጥቂዎች ተባባሪዎችን ለመለየት እየሰራ ነው ብለዋል ፑቲን ሲል RT ዘግቧል።

መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply