
ፑቲን እና ዢ ጂንፒንግ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ቻይና ባቀረበችዉ የሰላም መግባቢያ ሀሳብ ዙሪያ መነጋገራቸዉ ተሰምቷል፡፡
የቻይናዉ ፕሬዝዳንት ወደ ሩሲያ ያረጉት ጉብኝት በአሜሪካ ዘንድ በበጎ አልታየም፡፡
የፕሬዝዳንት ዢ ጅንፒንግ ጉብኝት ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን እያረጉ ላለዉ የጦር ወንጀል ዲፕሎማሲያዊ ሽፋን ለመስጠት የተደረገ ጉዞ ነዉ ብላለች አሜሪካ፡፡
ቻይና አመት ለዘለቀዉ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እራሷን የሰላም አምጪ አድርጋ እንደምትመለከት ገልጻለች፡፡
ፕሬዝዳንት ዥ ጅንፒንግ ወደ ሩሲያ ያደረጉት ጉዞ ሁለቱን አገራት የበለጠ ያቀራረበ እና የምዕራቡን ጫና ለመቋቋም በጋራ የሚሰሩበት እንደሆነ መናገሯን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡
አሜሪካ የሁለቱ ሃገራት ወደ ሰላም መምጣት በእጅ አዙር ሩሲያን ለማዳከም የምታደርገውን ጥረት በአጭር የሚቀጭ ነው፤ሰላሙ የሚመጣው በተገዳዳሪዋ ቻይና በኩል መሆኑ ደግሞ ይበልጥ እንዳስቆጣት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ቻይና ቀደም ሲል በባላንጣነት ሲተያዩ የነበሩትን ሳውዲአረቢያና ኢራንን ወደ ማስማማቷ ይታወሳል፡፡
በእስከዳር ግርማ
መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን
Source: Link to the Post