
ፑቲን ከሳልቫኪር ጋር መከሩ።
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ፑቲን ደቡብ ሱዳን ሉአላዊና ነጻነቷ የተጠበቀ ሀገር እንድትሆን ሩሲያ ድጋፍ እንደምታደርግም አረጋግጠዋል፡፡
ፑቲን አክለው እንደተናገሩትም ከደቡብ ሱዳን ጋር በደህንነት እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር በበኩላቸው፣ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ፑቲንን አመስግነው፡ በሞስኮ በተደረገው የአፍሪካ ሩስያ ጉባኤ ላይ በተስማማናቸው ስምምነቶች መሰረት ከሞስኮ ጋር አብረን እንሰራለን ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት፣ በጎረቤታቸው ሱዳን የቀጠለው ጦርነት እንዳይስፋፋ በመስጋት ነው ተብሏል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video
Source: Link to the Post