ፒያሳ ማዘጋጃ ቤት እና ቸርቸር ጎዳና መነሻቸው የነበሩ የታክሲ መሳፈሪያ ተርሚናሎች ሊቀየሩ ነው።ከዚህ ቀደም ፒያሳ መዘጋጃ ቤት እንዲሁም ቸርቸር ጎዳና ጫፍ መነሻቸውን ያደርጉ የነበሩ የታክሲ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/plY5_NGyh0ucyiGoPPCe8ZOBnPgiLLfMSxwLBYa0cPrCAWtj1z17Zs0mPM2uWWhDwsek1-8OVhkc_LXJFvllhy09p53JRholPoeOM2Ip6aq1rCaJUt5e8mYKN9haxbUqDKP5ol1z22s6uuhoY1-xKF-8L9XXsONc_7dIJxPdkws_jjBtnl-Y6uck-1JLkh0KVxrx68mWn4ulb2s3kQjIZW02bt6mZcF9qfDJ6frIxcrp0XDxiwe4aeL0xiGx6TEV0WNvbOBXKJN34UGs-K5-4ydbdI5IEHaX5Oz8fJbHD4Gh0VQfdUv3RDEStgRTLuf9LbflOL9ZWHb80XD_PkvYaw.jpg

ፒያሳ ማዘጋጃ ቤት እና ቸርቸር ጎዳና መነሻቸው የነበሩ የታክሲ መሳፈሪያ ተርሚናሎች ሊቀየሩ ነው።

ከዚህ ቀደም ፒያሳ መዘጋጃ ቤት እንዲሁም ቸርቸር ጎዳና ጫፍ መነሻቸውን ያደርጉ የነበሩ የታክሲ ተራዎች ከነገ ጥቅምት 01 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሊቀሩ መሆኑ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

ከመነሻው “ወደ ሳሪስ፣ ቦሌ፣ አደይ አበባ፣ ቦሌ ሚካኤል፣ ጎፋ መብራት ሃይል የሚሳፈሩ ተሳፋሪዎች ቦታ የተለወጠ መሆኑን እንድታውቁት ብሏል ቢሮው።

በዚህም ከነገ ጀምሮ የመነሻ ስፍራው አፍሪካ ህብረት ትምህርት ቤት ወይም አትክልት ተራ የአየር ጤና ታክሲ መያዣ ጋር ሲል ባሰራጨው ደብዳቤ ገልጻል።

የታክሲ መሳፈርያ ቦታው የተቀየረው ፒያሳ አራዳ ህንጻ አጠገብ የነበሩ ቤቶች መነሳታቸውን ተከትሎ ነበር።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply