ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአትክልት ተራ የሙዝ ማብሰያ መጋዘኖችን የማሸግ እርምጃ እየተወሰደ ነው ተባለ፡፡ኢትዮ ኤፍ ኤም በምስል የተደገፉ ከአካባቢው በደረሰው ቅሬታ መሰረት ከንግድ ቢሮ ነው…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/upLAHSai1ku03e3Brs0yv7gnIHeTC6E39Sn9G75ZGTQNZ90MNvp5jgOeZoRAKfTdbVyYetdV9u-CZSXVBEB86HvjfP5BcOo0F8MMIMwWZxQUxLxwCgQwVsgEGMb6aDKNhv80_DpnTuXDplvVtReaxV4Mv0cdS7bKEI9t3aqHFAe8x7Pnhqj8YIyQuq_hAUvRDS27lfOsTc3uyEgiqtHBDvSmANPArRkEj7uHeaZiIjDJjJb8-Trlf2Vt5TVXaIgT94z9zH4lLhcwmJ_gs22tE74tAmNE5j2fcnh8i0_RgYVFDxpnV-2qgiuCzCU3LW3eaAlIf2CEwLpIfO9zOIjJuA.jpg

ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአትክልት ተራ የሙዝ ማብሰያ መጋዘኖችን የማሸግ እርምጃ እየተወሰደ ነው ተባለ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም በምስል የተደገፉ ከአካባቢው በደረሰው ቅሬታ መሰረት ከንግድ ቢሮ ነው የመጣነው ያለ ግብረሃይል፣ የሙዝ ማብሰያ መገዘኖች የማሸግ እርምጃ ወስዷል፡፡

ከዚህ ቀደም የቃል ማስጠንቀቂያ ብቻ የደረሳቸው መሆኑን የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቦታውን እንዲለቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸው እንደነበርም ነግረውናል፡፡

መጋዘኖቹ የሙዝ ማብሰያ ቦታዎች በመሆናቸው ወዲያው ሊበላሹ የሚችሉ በየመደቡ ከ3መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ላይ የማሸግ እርምጃ መወሰዱ ተገቢ አይደለም ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ አልደረሰንም ያሉት ባለመጋዘኖቹ፣ ግብረሃይሉ በዚህ መልኩ እርምጃ መውሰዱ እንዳሳዘናቸውም ገልጸዋል፡፡

በዚሁ ጉዳይ የወረዳውን ስራ አስፈፀሚ ምላሽ ለማካተት ሙከራ ያደረግን ቢሆንም ዕለቱ የባለጉዳዮች ማስተናገጃ ቀን ነው በሚል ምላሽ ባለመስጠታቸው ሃሳባቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡
በቀጣይ የወረዳው ስራ አስፈፃሚ ምሻቸውን እንደሰጡን ሌሎችንም ጉዳዮች ጨምረን የምናቀርብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply