ፓርላማው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡለትን ሹመቶች በነገው ስብሰባው ሊያጸድቅ ነው 

በሃሚድ አወል

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚያቀርቧቸውን የአስፈጻሚ አካላትን ሹመት ለማጽደቅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ማክሰኞ ስብሰባ ሊያደርግ ነው። ሁለት የፓርላማ አባላት የነገው አጀንዳ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርቧቸውን ተሿሚዎች ሹመት ማጽደቅ” መሆኑን የሚገልጽ መልዕክት እንደደረሳቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። 

የተወካዮች ምክር ቤት ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ ባሰራጨው መረጃም  ነገ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ በሚካሄድ ስብሰባ ፓርላማው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረቡ ሹመቶችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ አስታውቋል። አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የፓርላማ አባል፤ በምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት በኩል የተላለፈው መልዕክት “ማንም የምክር ቤት አባል እንዳይቀር” የሚል ማሳሰቢያ መያዙን አክለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ተፈሪ ፍቅሬም እንደዚሁ ከኃላፊነታቸው መሰናበታቸው መገለጹ ይታወሳል። ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከሶስት ሳምንት በፊት ሹመት ከሰጧቸው አስራ አራት አምባሳደሮች መካከል አቶ ኡመር ሁሴን እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ይገኙበታል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

The post ፓርላማው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡለትን ሹመቶች በነገው ስብሰባው ሊያጸድቅ ነው  appeared first on Ethiopia Insider.

Source: Link to the Post

Leave a Reply