ፓርላማው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትንና የምክትላቸውን ሹመት አጸደቀ

https://gdb.voanews.com/01000000-0a00-0242-a69c-08db352b0bb0_w800_h450.jpg

የቀድሞውን የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ያለመከሠሥ መብት አነሣ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፤ ወ/ሮ ዘሃራ ዑመርን ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል።

ወ/ሮ ሌሊሲ ደሳለኝ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩ ሲኾን፣ ወ/ሮ ዘሃራ ዑመር ደግሞ፣ በሶማሌ ክልል በተለያዩ ደረጃዎች፣ በዳኝነት እና በሌሎችም ሕግ ነክ አገልግሎቶች ያገለገሉ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ፣ የቀድሞ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የነበሩትን የተወካዮች ምክር ቤት አባል፣ ዶር. ጫላ ዋታ ያለመከሠሥ መብት አንሥቷል፡፡

ያለመከሠሥ መብታቸው የተነሣው ዶር. ጫላ፣ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት፣ ፈጽመዋቸዋል በተባሉ የተለያዩ የሙስና ተግባራት፣ በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፤ በሚል፣ የፍትሕ ሚኒስቴር ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ እንደኾነ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

ዶር. ጫላ ዋታ፣ ያለመከሠሥ መብታቸው በእንደራሴዎች ምክር ቤቱ መነሣቱን ተከትሎ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply