ፓርቲና መንግስት የተለያዩ ስለመሆናቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ የሚሰጡ 10 ሺ ወጣቶች መመልመላቸውን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ነጻና ፍትሀዊ እንዲሆን ለማድረግ ከተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡የሰላም ሚኒስቴር የሰላም አስከባሪ ሰራተኛ አቶ አብዲ ዘነበ ለአሐዱ እንደተናገሩት ምርጫን ዲሞክራሲያዊ የማድረግ ሂደት ከተቋማት ጋር ካለው አቅም ጋር አብሮ የሚመጋገብ ሲሆን መዋቅርን የመገንባት ስራ በአንድ ግዜ የሚሰራ አይደለም ብለዋል፡፡

ምርጫን ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ በአንድ ጊዜ የሚመጣ ለውጥ አይደለም ተብሎም ስለማይተው ፓርቲን ከመንግስትና ከአገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዴት መለየት ይቻላል የሚል መዋቅር ለመዘርጋት እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ሰላም ሚኒስቴርም መንግስት ከፓርቲ የተለየ መሆኑን ለማሳወቅ በሀገር አቀፍ ደረጃ 10 ሺ በጎ ፍቃደኞችን በመመልመል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

እነዚህ ወጣቶች የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት የመንግስትና የፓርቲ መለያየትን  ለማህበረሰቡ ሚያስገነዝቡ ናቸው ያሉት አቶ አብዲ ዲሞክራሲን ማስፈን የገዥው ፓርቲ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የተፊካካሪ ፓርቲ አባላትም ጭምር በመሆኑ እነርሱም የድርሻቻውን ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ቀን 04/07/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply