ፕሪምየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ከሰበታ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ጀመረ

ፕሪምየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ከሰበታ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ከሰበታ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ዛሬ ጀምሯል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ድሬዳዋ ከሰበታ ከተማ ያለግብ 0 ለ 0 ተለያይተዋል።

በወጣው መርሃግብር መሰረት 9 ሰአት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፋሲል ከነማ ይጫወታል፡፡

ነገ እሁድ ከቀኑ 4 ሰዓት ደግሞ  ኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ ከተማ የሚጫወት ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ከሰዓት በኋላ ባለው ፕሮግራም 9 ሰዓት ላይ ጅማ ከተማ ከአዳማ ከተማ በአዲስ አበባ ስታድየም ይገናኛሉ።

እንዲሁም ሰኞ ረፋድ 4 ሰዓት ላይ ወላይታ ዲቻ ከሀዲያ ሆሳዕና፤ ቀን 9 ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና ይጫወታሉ፡፡

ሁሉም ጨዋታዎች በአዲስ አበበ ስታዲየም ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ፕሪምየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ከሰበታ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ጀመረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply