ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ከሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋር ተወያዩ

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ከሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሴቶች ወር አከባበርን በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ እና ታዋቂ ከሆኑ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋር በመወያየት ጀምረውታል፡፡

ስኬታማ ሴቶች በኢትዮጵያ የሚገኙ ወጣት ሴቶችን በመደገፍና በማበረታታት ረገድ ቁልፍ ሚና እንዳላቸው በዚህ ወቅት ተነስቷል፡፡

ተሳታፊዎቹም በፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ በተጀመሩ የተለያዩ መርሀ ግብሮች ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የዜቶች ወር በመጪው ወር ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀት ተጨባጭ የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማፍለቅ ታቅዶ የተጀመረ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ከሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply