ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጊኒ ገብተዋል

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጊኒ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ትናንት ማምሻውን ጊኒ ኮናክሪ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኮናክሪ ሲደርሱም የጊኒው ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ አቀባበል አድርገውቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የጊኒው ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት ነው ኮናክሪ የገቡት።

 

ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ በዚህ ዓመት በጊኒ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለሶስተኛ ዙር ማሸነፋቸውም ይታወሳል።

ጊኒ ከኢትዮጵያ ጋር ስትራቴጂክ አጋርነት ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ባለፉት 2 ዓመታት በሁለቱ ሀገራት መካከል በመሪዎች ደረጃ በተደረጉ የጉብኝት ልውውጦች በርካታ ስምምነቶች ተፈርመዋል።

ከነዚህም መካከልም የጤና፣ የግብርና፣ የቱሪዝም እና የተማረ የሰው ኃይል ልውውጥ የትብብር ስምምነቶች ይገኙባቸዋል።

ጊኒ እኤአ በ2014 በኢቦላ ወረርሽኝ በተጠቃችበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ሀገሪቱ ተልከው ማገልገላቸው ይታወሳል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጊኒ ገብተዋል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply