ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህዳሴው ግድብ ላይ የሰጡት አስተያየት የሚወገዝና ተቀባይነት የሌለው ነው – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህዳሴው ግድብ ላይ የሰጡት አስተያየት የሚወገዝና ተቀባይነት የሌለው ነው – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴው ግድብ ላይ የሰጡት አስተያየት የሚወገዝና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ ገለጹ፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ የፊታችን ሃሙስ የሚከበረውን 1 ሺህ 495ኛው የመውሊድ በዓል ምክንያት በማድረግ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሰጡትን አስተያየት አውግዘዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱ አስተያየትም ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቱ ሃጂ ዑመር ነብዩ መሀመድ በምድር ቆይታቸው በጎ ነገሮችን ሰርተው ማለፋቸውንም ገልጸዋል፡፡

በበዓሉ ለሰላት ወደ መስጊድ የሄዱ ምዕመናን ባለመጨባበጥና ርቀትን በመጠበቅ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠብቁም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው ኢትዮጵያውያን መተዛዘን፣ አብሮ መብላት እና መረዳዳት እንጅ መገዳደል ባህላቸው እንዳልሆነም አንስተዋል፡፡

ከዚህ አንጻርም አንዱ አንዱን መግደል ሊቆም፤ መጠፋፋት ሳይሆን ለሰላም በአንድነት መቆም ይገባልም ነው ያሉት፡፡

በፈቲያ አብደላ

The post ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህዳሴው ግድብ ላይ የሰጡት አስተያየት የሚወገዝና ተቀባይነት የሌለው ነው – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply