ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን “ግዳጃቸውን በጀግንነት እየተወጡ” ላሉ የሠራዊታቸው አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ፕሬዝደንቱ ሌሊት ላይ በቴሌቪዥን ቀርበው፤ በዩክሬን “ግዳጃቸውን በጀ…

https://cdn4.telesco.pe/file/g3cTwFlnOFOjfAtRnHPZnLGS9A73oqmKuFxLJlaebB3KuL0vmejZF6aRActJUER4km2NmSdOTQ0ZPIXi_TTLwUVRYxAB7N9FosNsJdChvkARtzrJO7r8e0Agxi4ajX8yrxX9U0BY6gvFrvOq5NaJ_lhkuqEROiRUy1vqyfXYcXuZe0aodbIlFAlJCU6PSCrYLjUv5RnzVltvdaBQbJOmKETsddSqMwTgtEsSxnkp_fxbXNplgc-RItOdpEf_nGEf6Thh60RiADBXqabJC45pTNfqXKDvmm-tOYFLcVCejBmlDD8O-bpyCpE9q1YWB6WSX855Ac3iq0khsL28j52nIw.jpg

ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን “ግዳጃቸውን በጀግንነት እየተወጡ” ላሉ የሠራዊታቸው አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ፕሬዝደንቱ ሌሊት ላይ በቴሌቪዥን ቀርበው፤ በዩክሬን “ግዳጃቸውን በጀግንነት እየተወጡ” ላሉ የሠራዊታችን አባላት ምስጋና ይድረሳችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

ፑቲን ለጦር አባላቱ “ፍጹም ለሆነው አገልግሎታችሁ በሩሲያ ሕዝብ እና በታላቋ አገር ስም ምስጋና እናቀርባለን”ብለዋል፡፡

ፑቲን አክለውም የጦሩ አባላት ለዶንባስ ሪፐብሊክ ሕዝቦች ድጋፍ የመስጠት ግዴታ ተጥሎባቸዋል ብለዋል።

ፕሬዝደንት ፑቲን በኪዬቭ ላይ ወረራ ከመክፈታቸው በፊት በምሥራቅ ዩክሬን በአማጺያን ለተያዙት ሁለት የዩክሬን ግዛቶች እውቅና መስጠታቸው ይታወሳል።

በሌላ ዜና አሜሪካን ጨምሮ እስካሁን ከ25 አገራት በላይ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ለመላክ ቃል ገብተዋል።

ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ኪንግደም ለዩክሬን ጦር መሳሪያ የላኩ አልያም ለመላክ ቃል ከገቡ አገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው እንደ ቢቢሲ ዘገባ።

እንዲሁም ግሪክ እና ስዊድን የጦር መሳሪያዎችን እና የሰብዓዊ እርዳታዎችን እንደሚልኩ አሳውቀዋል፡፡

እስካሁን በዚህ ጦርነት 352 ያህል የዩክሬን ዜጎች ሲሞቱ ከሟቹቹ መካከል 14 ህጻናት ይገኙበታል ሲል የዩክሬን ጤና ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

ከ422 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ድንበር አቋርጠው መሄዳቸው ተነግሯል፡፡

ያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply