ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ የመሪዎች ጉባኤ ወደ ሚካሄድበት ስፍራ እንዳይገቡ በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ክልከላ ለማድረግ ቢሞክሩም ኋላ ላይ ግን በስብሰባው ለመሳተፍ መቻላቸውን ተናግረዋል…

ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐሙድ የመሪዎች ጉባኤ ወደ ሚካሄድበት ስፍራ እንዳይገቡ በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ክልከላ ለማድረግ ቢሞክሩም ኋላ ላይ ግን በስብሰባው ለመሳተፍ መቻላቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ዛሬ ጠዋት በዝግ በሚካሄደው የኅብረቱ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ካረፉበት ሆቴል ለመውጣት በሞከሩበት ጊዜ “ኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች መንገድ ዘግተው ከሆቴሉ እንዳልወጣ አድርገዋል” በማለት ከሰዋል።

ነገር ግን በሌላ አገር ፕሬዝዳንት መኪና ከሆቴሉ ወጥተው ወደ ስብሰባው ቦታ መድረስ ቢችሉም “ጠመንጃ የታጠቁ ወታደሮች ከፊታችን ሆነው ወደ ኅብረቱ ጊቢ እንዳንገባ አግደውን ነበር” ብለዋል።

እንደ አስተናጋጅ አገር በቆይታቸው ለእንግዶቹ ደኅንነት ኃላፊነት እንዳለበት የገለጸው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የሶማሊያ ልዑካን በመንግሥት የተመደቡላቸውን የፀጥታ ሠራተኞች አንቀበልም ከማለታቸው በላይ፣ ጠባቂዎቻቸውም የጦር መሳሪያ ታጥቀው ወደ አፍሪካ ኅብረት ለመግባት ሲሞክሩ በኅብረቱ የፀጥታ አካላት መከልከላቸውን ገልጿል።

በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት የፕሬዝዳንቱን እና የልዑካኑን ደኅንነት ከመጠበቅ ባሻገር በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ እንዳላደናቀፈ እንዲሁም ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊዜ እንዳይገቡ እንዳልከለከለ አሳውቋል።

በአባቱ መረቀ

የካቲት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply