ፕሬዝዳንት ባይደን ለቀጣዩ ምርጫ ብቁ አይደሉም በሚል ከዲሞክራቶች ጥያቄ ተነስቶባቸዋል።

ዲሞክራቶችን ወክለው በቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከትራምፕ ጋር የሚፋጠጡት ጆ ባይደን አሁን ያሉበት ሁኔታ ለውድድሩ ብቁ አይደሉም ተብሏል።

የዲሞክራቶች አባላት በዚሁ ሁኔታቸው ትራምፕን ሊያሸነፉ እንደማይችሉ እየገለፁ ነው።

በመሆኑም ባይደን ከውድድሩ እራሳቸውን አግልለው ሌላ ፖለቲከኛ ፓርቲውን ወክሎ እንዲኸዳደር ጠይቀዋል።

ባለፈው ሳምንት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ክርክር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ባይደን ለመናገር ሲቸገሩ መታየታቸውን ተከትሎ የጤናና የዕድሜ ጥያቄ ተነስቶባቸዋል።

በዚያ ክርክር በትራምፕ ሙሉበሙሉ ተበልጠው ታይተዋል።
ይህንንም ተከትሎ ዲሞክራቶች እሳቸውን ተክቶ አትራምፕ ጋር የሚፎካከር ብርቱ ሰው እንዲሰየም መጠየቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply