
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጉዳይ አስፈጻሚ ደረጃ የሚገኘውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲን የሚመሩ ከፍተኛ ዲፕሎማትን በዕጩነት ማቅረባቸውን ጽሕፈት ቤታቸው ገልጿል። ፕሬዝዳንት ባይደን አገራቸውን በመወከል በተለያዩ አገራት የሚያገለግሉ በርካታ ዲፕሎማቶችን በእጩነት ባቀረቡበት ዝርዝር ውስጥ በኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲሆኑላቸው ኧርቪን ጆዜ ማሲንጋን ማቅረባቸውን ዋይት ሐውስ አስታውቋል።
Source: Link to the Post