ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ቁጣ በርትቶባቸዋል፡፡አሜሪካዊያን በፕሬዝዳንታቸው ላይ ከፍተኛ ቁጣ በማሰማት ላይ ናቸው፡፡ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአስተዳደራቸው እና በግል አቋማቸው ምክንያት በህዝባቸው…

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ቁጣ በርትቶባቸዋል፡፡

አሜሪካዊያን በፕሬዝዳንታቸው ላይ ከፍተኛ ቁጣ በማሰማት ላይ ናቸው፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአስተዳደራቸው እና በግል አቋማቸው ምክንያት በህዝባቸው ዘንድ አመኔታ እያጡ ነው የሚባሉት ጆ ባይደን አሁን ቁጣ አዘል ትችት እየቀረበባቸው ይገኛል፡፡

በሀገሪቱ እየተከናወነ ያለ ጉዳይ በቅርበት አያውቁም የሚሉት ተቺዎቻቸው ስልጣን ይልቀቁ እስከማለትም ደርሰዋል፡፡

በተለይም ከሰሞኑ የመከላከያ ሚኒስትራቸው በጠና መታመማቸው ፕሬዝዳንቱ እንደማያዉቁ እና ሆስፒታል የመግባታቸው ወሬም እንዳልሰሙ መነገሩ ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡

ይህ ጉዳይ አሜሪካዊያን ፕሬዝዳንቱ ቸልተኝነታቸው ከልክ በላይ ሆኗል እናም ስልጣናቸው ያስረክቡ እንዲሉ ምክንያት ሆኗል፡፡

የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሊዮድ ኦስቲን ባሳለፍነው ሳምንት በጸና ታመው ሆስፒታል መግባታቸው ይታወሳል፡፡

ሚንስትሩ በጸና ታመው ለአራት ቀናት የጽኑ ህክምና ክትትል ውስጥ በቆዩባቸው ቀናት ፕሬዝዳንት ባይደንን ጨምሮ የሀገሪቱ ዋና ዋና ባለስልጣናት እንደማያውቁም ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም ሚንስትሩ ያጋጠማቸው ህመም ምን እንደሆነ ለመንግሥታቸው እና ለህዝብ ሳይነገር መቆየቱ አሜሪካዊያንን ማስቆጣቱ ተገልጿል።

ግፊቱ እየጨመረ ሲመጣም ህክምናውን ለሚንስትሩ የሰጠው ዋልተር ሪድ ሆስፒታል ሊዮድ ኦስቲን በፕሮስቴት ካንሰር መጠቃታቸውን እና ህክምና እንዳደረገላቸው ይፋ አድርጓል።

የ70 ዓመቱ ጡረተኛው የአሜሪካ ባለ አራት ኮኮብ ጀነራል ሊዮድ ኦስቲን በካንሰር መጠቃታቸውን ፕሬዝዳንት ባይደን ሳይቀር እንደማያውቁ ሮይተርስ ዘግቧል።

ሔኖክ ወ/ገበርኤል

ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply